የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የሎተሪ ሽልማት

ሰኔ 26 ቀን 2013 ዓ.ም   ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የቁጠባ ባህልን ማሳደግ ለባንካችንም ሆነ ለሀገራችን የሚሰጠው ከፍተኛ ጠቀሜታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ከሚሰጣቸው የባንክ አገልግሎቶች ጎን ለጎን አገልግሎቶቹን በስፋት ለሚጠቀሙ ደንበኞቹ በርካታ የማበረታቻ ሽልማቶችንም በሎተሪ ዕጣ መልክ ሲሸልም ቆይቷል፡፡ የማበረታቻ ሽልማቶቹን ከጊዜ ወደ ጊዜ በአይነት፣ በብዛትም ሆነ በጥራት እያሻሻለ ዕድለኞችን ተጠቃሚ ማድረጉን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡   ሰኔ 25 […]

የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ እንሸላለም (ይቆጥቡ ይሸለሙ እና የሉሲ “የሴቶች” የቁጠባ ሂሳብ) የጎዳና ቅስቀሳ አካሄደ

የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ እንሸላለም (ይቆጥቡ ይሸለሙ እና የሉሲ “የሴቶች” የቁጠባ ሂሳብ) የጎዳና ቅስቀሳ ማካሄዱን ከገበያ ጥናትና ቢዝነስ ማስፋፊያ መምሪያ የተገኘው መረጃ አመለከተ፡፡ ከአዲስ አበባ ከተማ የተነሳው የቅስቀሳ ቡድን ሰበታ፣ ወሊሶ፣ ወልቂጤ፣ ግቡሬ፣ እምድብር፣ አረቅጥ፣ ቡታጅራ፣ ወራቤ፣ ሌራ፣ ሆሳዕና፣ ዶዮ ገና፣ ሻሸመኔ፣ ሐዋሳና ሌሎችም ከተሞችን በማዳረስ የይቆጥቡ ይሸለሙ እና ሉሲ የሴቶች ቁጠባ ሂሳብ የጎዳና ቅስቀሳ ሥራ […]

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የተለያዩ የአገልግሎት ክፍያዎችን መፈጸም የሚያስችል ዘመናዊ አሠራር በሥራ ላይ አዋለ

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከጊዜ ወደ ጊዜ አሠራሩን በማዘመን እና የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት እንዲሁም ዘመን ባፈራቸው ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ ደንበኞቹንና አገልግሎት ፈላጊዎችን ለማርካት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ባንኩ፣ አገልግሎቶቹን ለደንበኞቹ ምቹና ቀልጣፋ ከማድረግ አኳያ የኢትዮ ቴሌኮም የባለ ገመድ ስልክ፣ የሞባይልና የብሮድ ባንድ ክፍያዎችን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቲኬት ክፍያ፣ ጉዞ-ጎ (የተለያዩ አየር መንገዶች የቲኬት ክፍያ)፣ የቀላል ትራንስፖርት ክፍያ፣  […]

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በትርፋማነቱ ቀዳሚ ከሚባሉ ባንኮች አንዱ ሆነ

የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ 21ኛው መደበኛ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ታህሳስ 15 ቀን 2013 ዓ.ም በኢንተርኮንትኔንታል አዲስ ሆቴል አዳራሽ በተካሄደበት ወቅት፤ ባንኩ በስትራቴጂክ ፕላኑ በአምስተኛው ዓመት ይደርስበታል ተብሎ የታቀደውን የትርፋማነት መስፈርት በ2 ዓመት ጊዜ ውስጥ በማሳካት 1.3 ቢሊዮን ብር አትርፎ በኢንዱስትሪው ውስጥ ካሉ ቀዳሚ ከሚባሉ የግል ባንኮች አንዱ መሆኑን አረጋግጧል፡፡ የአገልግሎት አሰጣጡን ከጊዜ ወደ ጊዜ በማሻሻልና ተደራሽነቱን […]

የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ

የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 21ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ሐሙስ ታህሳስ 15 ቀን 2013 ዓ.ም. ከጧቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ ካዛንቺስ አካባቢ በሚገኘው ኢንተርኮንቲነንታል አዲስ ሆቴል አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም፣ የባንኩ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም በሕጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካኝነት በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በጉባዔው እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል፡፡ የ21ኛው መደበኛ ጉባኤ አጀንዳዎች፡- የጉባዔውን ድምፅ ቆጣሪዎች መሰየም፣ ምልዓተ […]

የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ

የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SBB/71/2019 በሚደነግገው መሠረት በ21ኛ የባለአክሲዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ እንደሚካሄድ ይታወቃል፡፡ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ማስታወቂያ በማውጣትና የጥቆማ ቅፅ በሁሉም የባንኩ ቅርንጫፎች በማሰራጨት ከሰኔ 15 ቀን 2012 ዓ.ም. እስከ መስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ የዕጩ […]

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ አስመዘገበ

በኢትዮጵያ የግል ባንኮች ታሪክ ቀደምት አሻራቸውን ካሳረፉት መካከል አንዱ የሆነው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ ከምስረታው ጀምሮ ለተከታታይ ሃያ ዓመታት የትርፍ መጠኑን እያሳደገ መጥቶ  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት (እ.አ.አ 2019/20) ከታክስና ከተለያዩ ቅንስናሾች በፊት ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ በማትረፍ በሀገሪቱ በትርፍ ቀዳሚ ከሚባሉ ባንኮች አንዱ መሆኑን በድጋሚ አረጋግጧል፡፡ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በአገርና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮረና ቫይረስ […]

ለንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አ\ማህበር ባለአክሲዮኖች በሙሉ

የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አ/ማ ዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምልመላና አስመራጭ ኮሚቴ ከሰኔ 15 ቀን 2012 ዓ.ም. እስከ መስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ የዳይሬክተሮች ቦርድ እጩ አባላትን ጥቆማ ይቀበላል፡፡  በመሆኑም የባንኩ ባለአክሲዮኖች ለባንኩ የላቀ ውጤት ለማበርከት ብቃቱ ያላቸውን በባንክ ሥራ አዋጅ ቁጥር 592/2008 እና 1159/2019 /የተሻሻለው/ በብሔራዊ ባንክ መመሪያ SBB/70/2019 እና SBB/71/2019 ላይ የተዘረዘሩትን የሚከተሉትን መስፈርቶች […]

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ተጨማሪ የብድር ወለድ ምጣኔ ቅናሽ አደረገ

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በዓለምና በአገር አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ወረርሽኝ በኢኮኖሚው ዘርፍ ላይ ያደረሰውን ጉዳት በመመልከት በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስክ የተሰማሩ የባንኩ ደንበኞችን ለመደገፍ በድጋሚ የብድር ወለድ ምጣኔ ቅናሽ አደረገ፡፡ በአገር ውስጥ ንግድ፣ በሕንጻና ኮንስትራክሽን፣ በአምራችነት፣ በአስመጪነት፣ በፕሮጀክት ደረጃ ላሉ ሆቴሎች፣ በትራንስፖርት፣ በማዕድን ኢነርጂና ውኃ፣ በግብርናና በግል ዘርፍ ለተሰማሩ የባንኩ ተበዳሪዎች እስከ ሶስት […]

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የወለድ ምጣኔ ቅናሽ አደረገ

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ በአገራችንና በዓለም አቀፍ ደረጃ በመስፋፋት ላይ የሚገኘው የኮረና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ወረርሽኝ በዜጎች ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ በመመልከት   የወለድ ምጣኔ ቅናሽ ማድረጉን አስታወቀ፡፡ በቫይረሱ ተጽዕኖ በከፍተኛ ደረጃ ተጎጂ በሆኑ የኢኮኖሚ  ዘርፎች ላይ ተሰማርተው የሚገኙ የባንኩ ተበዳሪዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት የባንኩ ቦርድና ከፍተኛ ሥራ አስፈጻሚ ባደረገው ስብሰባ፦ ለሆቴልና ቱሪዝም፣ ለአስጎብኚ ድርጅቶች፣ […]