Internet Banking
Internet Banking

ታታሪውን ባንካችን ወደ ደንበኞቹ ይበልጥ ለመቅረብ  “በአዲስ መንፈስ ለላቀ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በክልል ከተሞች የማርኬቲንግ ንቅናቄ እያከናወነና ውጤታማ የገበያ ትስስር እየፈጠረ ይገኛል፡፡

 

በዚሁ መሰረት በሆሳዕና ዲስትሪከት ስር በቡኢ፣ ኬላ፣ ቡታጀራ፣ ኢንሴኖ፣ ማረቆ ቆሼ፣ ቦዠባር፣ አገና፣  ጉብሬ፣ ወልቂጤ፣ ወራቤ፣ ፎንቆ፣ ሆሳዕና፣ ሀደሮ፣ ወላይታ፣ ሁንቦ፣ ብርብር፣ አርባምንጭ እና አርባምንጭ ዙሪያ አዳዲስ ደንበኞችን በማፍራት ባንኩን የማስተዋወቅ ሥራ ተሠርቷል፡፡

 

በሐዋሣ ዲስትሪክት ስር ሻሸመኔ፣ ሐዋሣ እና አካባቢው፣ ዲላ፣ ይርጋጨፌ፣ ይርጋለምና አለታወንዶ በሌላ በኩል በደቡበ ምሥራቅ  አዲስ አበባ ዲሰትሪክት ስር በአዳማና በሞጆ ከተሞች አዳዲስ ደንበኞች የማፍራትና ነባር ደንበኞችን የማወያየት ሥራ ተከናውኗል፡፡

 

የማርኬቲንግ ንቅናቄውን እንቅስቃሴ በከፊል የሚያሳዩ ምስሎችን በዚህ ማስፈንጠሪያ https://www.nibbanksc.com/gallery/ መመልከት ይችላሉ፡፡

NIB BANK

NIB BANK

Committed To Services Excellence

Share this post with

You May Also like

Reports

Jobs