Internet Banking
Internet Banking

የባለአክሲዮኖች 20ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

ለተከበራችሁ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አክሲዮን ማኅበር ባለአክሲዮኖች፡-

የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች 20ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 366፣ 367፣ 370፣ 371፣372 እና በተሻሻለው የባንኩ መመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 16 መሰረት ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ከጧቱ 230 ጀምሮ ቦሌ አካባቢ በሚገኘው በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም፣ የባንኩ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም በሕጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካኝነት በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል፡፡

  • የባንኩ የተፈረመ ካፒታል 10,000,000,000.00
  • የባንኩ የተከፈለ ካፒታል 7,077,947,000.00
  • የባንኩ የምዝገባ ቁጥር  KK/AA/02/0000814/2004
  • የባንኩ አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ፣ ልደታ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 09 ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ህንጻ

የ20ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች፡-

ድምጽ ቆጣሪዎች ተለይተው ምልአተ ጉባኤው መሟላቱ ከተረጋገጠ በኃላ፡-

  1. የጉባዔውን አጀንዳዎች ማጽደቅ፣
  2. እ.ኤ.አ በ2022/23 ሂሳብ ዓመት በባንኩ የተገኘው የትርፍ ድርሻ ላይ ውሳኔ ያልተሰጠበት የትርፍ ድርሻ ለካፒታል ማሳደግ በሚውልበት ሁኔታ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ፤
  3. የባንኩን የተከፈለ ካፒታል ለማሳደግ በ18ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የተወሰነውን የካፒታል ማሳደጊያ ጊዜ በሚሻሻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ፤
  4. የባንኩን ካፒታል ማሳደግ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ፤
  5. የጉባዔውን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ፣

ማሳሰቢያ፡-

  • ባለአክሲዮኖች በጉባዔው ለመገኘት ኢትዮጵያዊነታቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ፣ መንጃ ፈቃድ፣ ፓስፖርት ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊነታቸውን የሚያረጋግጥ መታወቂያ ዋናውን ከፎቶ ኮፒ ጋር ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡
  • በውክልና የሚገኙ ከሆነ የወካዩን ባለአክሲዮን ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ዋናውን ከኮፒ ጋር ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡
  • ውክልና መስጠት የሚፈልግ ባለአክሲዮን ከመጋቢት 5 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በስራ ሰዓት ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ፣ መንጃ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ይዞ ሰንጋተራ በሚገኘው የባንኩ አዲሱ ዋና መ/ቤት ህንጻ ምድር ወለል ለዚሁ በተዘጋጀው ቦታ በግንባር በመቅረብ የተዘጋጀውን ቅጽ በመሙላት መወከል ይችላል፡፡
  • በሠነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጄንሲ ወይም አግባብ ባለው አካል በተሰጠ ውክልና በስብሰባ ላይ የሚገኝ ተወካይ የወካዩን ባለ አክሲዮን ኢትዮጵያዊነት ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊነት የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ዋናውን ከኮፒ ጋር እና የውክልናውን ዋና ከኮፒ ጋር ይዞ መገኘት ይኖርበታል፡፡

የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ

NIB BANK

NIB BANK

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

News

ታታሪውን ባንካችን ወደ ደንበኞቹ ይበልጥ ለመቅረብ  “በአዲስ መንፈስ ለላቀ ከፍታ”

Read More

You May Also like

Reports

Jobs