ባንኩ የ2025/26 በጀት ዓመት አመታዊ የማኔጅመንት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መርሐ ግብሩን “ጉዞ ወደ 2030 ለላቀ ስኬት” በሚል መሪ ቃል ዛሬ ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም የባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ ከፍተኛ የማኔጅመንት አመራሮች፣ የመምሪያና የዲስትሪክት ዳይሬክተሮች እንዲሁም ሁሉም የባንኩ የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች በተገኙበት በባንኩ ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ በድምቀት እያተካሄደ ይገኛል።
የግምገማ መርሐ ግብሩን በይፋ የከፈቱት የባንኩ የዱሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሺሰማ ሸዋነካ፣ ለታዳሚዎች “እንኳን ደህና መጣችሁ፣ ውይይቱ የተሳካና ውጤታማ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ” የሚል መልእክታቸውን አስተላፈዋል።
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደ በበኩላቸው በግምገማ መርሃ ግብሩ ታቅደው በነበሩ ዋና ዋና ተግባራት አፈጻጸም እንዲሁም ድክመቶቻችንን በማረም ለጀመርነው የ2026/2027 በጀት ዓመት በሁሉም መለኪያዎች የላቀ ስኬት የምናስመዘግብበትና ሁሉም ባለድርሻ አካል የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በመወጣት ባንኩን ወደ ተሻለ ከፍታ የምናደርስበት ይሆናል ብለዋል፡፡
መርሐ ግብሩ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን የ2026/27 በጀት አመት ዋና ዋና ተግባራትና የትኩረት ነጥቦች የሚዳሰሱ ይሆናል።
***
ይሠሯል ከልብ እንደ ንብ!




