ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ ሆሳዕና ከተማ ዙሪያ፣ ኤጦ ቀበሌ ነዋሪ ለሆኑ እናቶች የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የበዓል ስጦታ አበረከተ፡፡
የበዓል ስጦታውን ያበረከቱት የባንካችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደ እና የክልሉ ፕሬዚዳንት እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ሲሆኑ የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞታቸውን በዚሁ መርሐ-ግብር ላይ አቅርበዋል፡፡
ባንኩ የተለያዩ በዓላትን ምክንያት በማድረግ አቅመ ደካማ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ ሲሆን ይህንኑ ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመርሐ-ግብሩ ላይ ተነግሯል፡፡
መልካም የገና በዓል!
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!
#Nib #nibbank #Mobilebanking #nibteraPOS








