ከዚህ ቀደም ከሁሉም የባንኩ ከፍተኛ አመራር ጋር ተመሳሳይ የውይይት መርሃ-ግብር በየደረጃው ሲያከናወኑ የቆዩት ዋና ሥራ አስፈጻሚው ዛሬ በዋና መሥሪያ ቤት ከዲቪዥን ሥራ አስኪያጆችና ኦፊሰሮች ጋር እያካሄዱት ያለው ውይይትም የዚያው አካል ነው፡፡
ውይይቱ ሁሉም ሰራተኛ በላቀ የሀላፊነት ስሜት ስራውን በማከናወን ባንኩ በተሻለ ቦታ እንዲገኝና የጋራ ውጤታማነትን መፍጠር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው፡፡
ከሰራተኞች፣ ከደንበኞችና ከሥራ ሃላፊዎች ጋር ሊኖር በሚገባ የተግባቦትና የአመራር ክህሎት ዙሪያም መሰረታዊ ግንዛቤዎችን ለማስጨበጥና ተነሳሽነትን ለማሳደግ ያለመ ነው፡፡
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!