ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ”10 ዓመታት በሃላል አገልግሎት!” በሚል መሪ ሃሳብ የ“ንብ ሃላል” ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መስጠት የጀመረበትን 10ኛ ዓመት ክብረ-በዓል ላለፉት ስድስት ወራት በተለያዩ ሁነቶች ሲያከብር ቆይቶ፤ የማጠቃለያ መርሃ-ግብሩን ዛሬ ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በዋና መስሪያ ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ በደማቅ ሁኔታ አጠናቋል።
በማጠቃለያ መርሃ-ግብሩ ላይ የባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ አባላት፣. ከፍተኛ አመራሮች፣ የባንኩ ደንበኞች እና ተጋበዥ እንግዶች ተገኝተው የ10 ዓመታት የስኬት ጉዞን በጋራ አክብረዋል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የንብ ሃላል የ10 ዓመታት የዕድገት ጉዞ፣ የደንበኞችና የተቀማጭ ገንዘብ ዕድገት እንዲሁም በቀጣይ ባንኩ አገልግሎቱን ከዚህ በላቀ መልኩ ለማሳደግ፣ በዲጂታልና ደንበኛ ተኮር በሆነ መልኩ የሚሰራ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ በተጨማሪም ለአገልግሎቱ እድገት አስተዋፅኦ ላበረከቱ ደንበኞች እና ሠራተኞች ልዩ ዕውቅና ተሰጥቷል።
በመጨረሻም አገልግሎቱ ስኬታማ እንዲሆን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ደንበኞች፣ ባለድርሻ አካላት እና ሠራተኞቹ ምስጋና የቀረበ ሲሆን በቀጣይም የሸሪዓ መርሆዎችን በተከተለ መንገድ ባንኩ ዘመናዊ እና ፈጠራን ያማከለ የፋይናንስ አገልግሎት እንደሚያቀርብ ተመልክቷል፡፡




