Internet Banking
Internet Banking

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከእማዋ ሾፒንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ጋር አብሮ ለመሥራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈራረመ

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከእማዋ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ዛሬ ጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም ተፈራረመ።

 

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከእማዋ ሾፒንግ ኩባንያ ጋር አብሮ በመሥራቱ ደስተኛ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በተለይም ባንኩ በኢትዮጵያ በፍጥነት በማደግ ላይ ባለው የንግድና የፋይናንስ ዘርፍ ላይ እያደረገ ያለውን ጉልህ የሆነ አወንታዊ አስተዋጽኦ አጠናክሮ እንደሚቀጥል እና እማዋ ሾፒንግ ኩባንያ ትልቅ የቢዝነስ ርዕይ ይዞ ወደ ሥራ የገባ በመሆኑ ባንካችንም የድርጅቱ ርዕይ ስኬታማ እንዲሆን በቁርጠኝነት የሚሠራ መሆኑ በመርሐ ግብሩ ላይ ተሰምቷል፡፡

 

የእማዋ ሾፒንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ባለቤትና ጄኔራል ማኔጀር አቶ ሰለሞን አየነው በበኩላቸው ኩባንያው ከንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ጋር በተለያዩ ዘርፎች አብሮ ለመሥራት በመቻሉ እጅግ ደስተኛ መሆኑን ገልጸው እማዋ ሾፒንግ ከባንኩ ጋር የጋራ የሚያደርገውን የማንነት (identity) ብራንድ ፈጥሮ ኢንተርናሽናል ስታንዳርድ ያለው ካምፓኒ ለመፍጠር ያለመውን ርዕይ ለማሳካት የሚሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡

 

እማዋ ሾፒንግ በርካታ ወጣቶች ተጠቃሚ የሚሆኑበት ትልቅ ኩባንያ መሆኑን ያመለከቱት አቶ ሰለሞን ገበሬው፣ ታዳጊ ማንፋክቸሪንግ ተቋማትና ልዩ ልዩ አቅራቢ ድርጅቶች ተጠቃሚ የሚሆኑበት መሆኑን አመልክተዋል፡፡

 

በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የባንኩ እና የእማዋ ሾፒንግ ኩባንያ ከፍተኛ የማኔጅመንት አካላት የተገኙ ሲሆን ባንካችንን በመወከልም የባንኩ ቺፍ ሪቴይልና ኤስኤምኢ ባንኪንግ ቺፍ ኦፊሰር አቶ ሙሉቀን ደምሴ የፊርማ ሥነ ሥርዓት አካሄደዋል፡፡

Picture of <p> <b>  <span style="color: #8B5E3C;">Nib International</span>   <span style="background: linear-gradient(to right, #8B5E3C, #FFA500); -webkit-background-clip: text; color: transparent; font-weight: bold;">     Bank   </span></b> </p>

Nib International Bank

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs