በስልጠና መርሐ ግብሩ ላይ የባንኩ የሰው ኃብት አስተዳደር ም/ቺፍ ኦፊሰር አቶ ዘውዱ ሀኪሙ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የኢትዮጵያ የሴቶች የፋይናንስ ባለሙያዎች ኔትዎርክ የቦርድ አባል እና የልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶክተር እመቤት መለሰ ራስን ስለማሻሻል ፣ ስለተግባቦት ችሎታ፣ ራስን ስለማክበር ፣ ኢሞሽናል ኢንተለጀንስ፣ የግል የልማት እቅድ እና ስኬትን ማክበር አስመልክቶ የማነቃቂያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የኔትዎርኩ አስተባባሪ ወ/ሮ ፂዮን ግርማም ስለ ኢትዮጵያ የሴቶች የፋይናንስ ባለሙያዎች ኔትዎርክ አጠቃላይ ገለፃ አድርገዋል፡፡
በስልጠና መርሐ ግብሩ ላይ የባንኩ የማኔጅመንት አካላትና ከ120 በላይ ተሳታፊዎች እና የኔትዎርኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን የመሪነት አቅምን ስለማሳደግና ሴቶችን ወደ ከፍታ በማምጣት ረገድ ለተሳታፊዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!






