ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከተለያዩ ተቋማት ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን ስትራቴጂካዊ ስምምነቶችን እየተፈራረመና እየሰራ ሲሆን ዛሬም ይህንኑ አጠናክሮ ለማስቀጠል ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር ተፈራርሟል፡፡
ሁለቱም ተቋማት ባደረጉት የፊርማ ሥነ-ስርዓት እንደተገለጸው፤ ባንኩ ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በሥራ ፈጠራ፣ በጤና እና በኢንተርፕራይዞች ዙሪያ ለመሥራት ማቀዳቸውን መሥሪያ ቤቶቹ በውይይታቸው ወቅት ተናግረዋል፡፡
በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በኩል ንግግር ያደረጉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ሲሆኑ፣ ከንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ጋር በተጠቀሱት ጉዳዮች ዙሪያ ለመሥራት የጋራ ጉዳይ በመሆኑ፤ ለአገራችን ዕድገት ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ገልፀው፤ ስምምነቱ በባንኩና በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ መካከል የሚኖረውን ግንኙነት ይበልጥ ሊያጠናክረው እንደሚችል እምነታቸው መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የባንካችን ዋና ሥራ አሥፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደም ዛሬ የተፈረመው ስምምነት በተግባር ሲተረጎም ፍሬው ያማረ እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ጠቁመዋል፡፡
በመጨረሻም ስምምነቱ በቅርብ ቀን ወደ ተግባር እንደሚገባ በፊርማ ሥነ- ስርዓቱ ተቋማቱ ገልጸዋል፡፡
***
ይሠሯል ከልብ እንደ ንብ!




