Internet Banking
Internet Banking

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ፤ ለእርሻ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት አርሶ አደሩን በማገዝ አብረው ለመስራት የሚያስችላቸውን ውይይት አካሄዱ፡፡

ባንካችን ከለእርሻ ጋር አብሮ ለመስራት የተፈራረሙትን የውል ስምምነት መነሻ በማድረግ፤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉመር ወረዳ 120 (አንድ መቶ ሀያ) ለሚደርሱ አርሶ አደሮች የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ የጀመሩትን ሥራ በማጠናከር ተጨማሪ 10,000 አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከክልሉ መንግሥት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡

በክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ቢሮ በተካሄደው ውይይት ላይ የመወያያ ሰነድ የቀረበ ሲሆን፤ በሰነዱ ላይም ሀሳቦች ተነስተው ማብራሪያና ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

የባንካችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደም በበኩላቸው፤ የባንካችን የ5 ዓመት ስትራቴጂካዊ ዕቅድ የትኩረት አቅጣጫ ከሆኑት ጉዳዮች አንዱ፤ የአርሶ አደሮችን አስተራረስ ዘዴ ለማዘመን ከሚሰሩ እንደ ለእርሻ ካሉ ድርጅቶች ጋር አብሮ በመሥራት ለሚያስፈልጋቸው የእርሻ ግብዓት ፋይናንስ ማመቻቸት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የለእርሻ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም እንድሪያስ ሲናገሩ ድርጅታቸው ዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም የአርሶ አደሩን ነባራዊ ሁኔታ ለማዘመን ከባለድርሻ ተቋማት ጋር አብሮ መስራቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

የክልሉ ር/መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) ንብ ኢንተርናሽናል ባንክና ለእርሻ የጀመሩትን ሥራ በውጤት ለማሳመር አስፈላጊው ድጋፍና ትብብር ከክልሉ መንግሥት እንደማይለያቸው በመጠቆምና መመሪያ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!

Picture of <p> <b>  <span style="color: #8B5E3C;">Nib International</span>   <span style="background: linear-gradient(to right, #8B5E3C, #FFA500); -webkit-background-clip: text; color: transparent; font-weight: bold;">     Bank   </span></b> </p>

Nib International Bank

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs