ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዘጋጅነት ዛሬ በአዲስ አበባ የሳይንስ ሙዚየም በይፋ በተከፈተው ፎረም ላይ በመሳተፍ አዳዲስ የዲጂታልና ነባር መደበኛ አገልግሎቶቹን “ንብ ተራ” በሚል ስያሜ ለተከበሩ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት አቶ ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዥ የተከበሩ አቶ ማሞ ምህረቱ፣ ለሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናትና የተለያዩ ባንኮች ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች በተገኙበት አስተዋውቋል፡፡
የፋይናንስ ፎረሙ ለሁለት ቀናት ማለትም ግንቦት 07 እና 08 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን ባንኮች፣ ኢንሹራንሶች፣ አነስተኛ የገንዘብ ተቋማት፣ የውጭ ምንዛሬ ቢሮዎች፣ የልማት አጋሮች እና ሌሎችም የታደሙ ሲሆን እርስዎም በፎረሙ እንዲሳተፉና እንዲጎበኙን ተጋብዘዋል፡፡
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!