ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከሁለቱ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የታክሲ አገልግሎት ሰጪዎች የኢንሹራንስ ክፍያቸውን ያለችግር በተመቻቸ ሁኔታ የሚከፍሉበትን ሥርዓት እንደተዘረጋ በፊርማ ሥነ ሥርአቱ ላይ ተገልጿል፡፡
የስምምነት ፊርማውን በንብ ኢንተርናሽናል በኩል አቶ ሙሉቀን ደምሴ – የባንኪንግ ኦፕሬሽንስ ቺፍ ኦፊሰር፣ በንብ ኢንሹራንስ ኩባንያ ወገን – አቶ ግሩም ፈቀደ የውል ሥራ አስፈጻሚ እና በጂቱጂ በኩል ደግሞ – አቶ ቴዎድሮስ መሐሪ የቴክኖሎጂ ቺፍ ኦፊሰር ፈርመዋል፡፡
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!