ባንካችን፣ በጉራጌ ዞን የእዣ ወረዳ መቀመጫ የሆነው የአገና ከተማን የውኃ ቢል ክፍያ ለማሰባሰብ የሚያስችል የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራረመ፡፡
ከጊዜ ወደ ጊዜ ተደራሽነቱን በማስፋትና አገልግሎቱን በማዘመን ላይ የሚገኘው ባንካችን ለደንበኞች ምቹና ቅርብ በመሆን ወርሃዊ ክፍያቸውን መፈጸም ያስችላቸዋል፡፡ ቀደም ሲልም ከተለያዩ መሥሪያ ቤቶችና ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመሥራት የስምምነት ፊርማ መፈራረሙ ይታወሳል፡፡