ታኅሣሥ 2 ቀን 2017 ዓ.ም በባንኩ አራት ኪሎ አዳራሽ በተከናወነው በዚህ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ የሚገኙ ሁሉም የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያ1ች ተሳትፈዋል፡፡
ዋና ሥራ አስፈጻሚው በዚሁ መድረክ ባደረጉት ንግግር ሁሉም የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች ከእቅዳቸው ትይዩና በላይ በመፈጸም ባንኩን ይበልጥ ተወዳዳሪና ውጤታማ ለማድረግ መስራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡
በእዚህም የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆችና ሰራተኞቻቸው ከሥራ ቦታ ተጋባቦት አንስቶ እስከ እቅድ አፈጻጸም ውጤታማነት ላይ ተኩረት በማድረግ እንዴት ስኬታማ መሆን እንደሚችሉ የሚያብራራ ገለጻ አድርገዋል፡፡
በመሰረታዊ የአመራር ክህሎትና ክፍተቶች ዙሪያ ያተኮረ አነቃቂ ንግግር ያደረጉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች ከሰራተኞቻቸው ጋር ብቻ ሳይሆን ከደንበኞች አገልግሎትና አያያዝ ጋር በተገናኘም ባንኩ ሊተገብረው ይገባል ያሉትን ቀልጣፋና ዘመናዊ አሰራር በተመለከተም አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡
በመድረኩ የተሳተፉት የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች በበኩላቸው በዋና ሥራ አስፈጻሚው የተዘጋጀው የማነቃቂያ መርሐ-ግብር የውስጥ ተነሳሽነትን ከማሳደግና ለውጤት ከመስራት አኳያ እጅግ ጠቃሚ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዚህም በስራቸው ከሚገኙ ሰራተኞች፣ ከዲስትሪክትና ዋና መስሪያ ቤት ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ባንኩን ወደላቀ ከፍታ ለማድረስ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
***
25 አመታትን በታታሪነትና በአገልጋይነት!