Internet Banking
Internet Banking

የንብ ባንክ አዳዲስ የክፍያ ሥርአት ማብሰርያ መርሐ ግብር ተካሄደ

የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ደንበኞች ሥራቸውን ለማቀላጠፍና ምቹ የክፍያ ሥርአት መፈጸም የሚያስችላቸውን ንብ አምበር ፔይ እና ንብ ፔይስትሪም የተሰኙ የዲጅታል አገልግሎት መተግበሪያዎች ማብሰርያ መርሐ ግብር ተካሄደ፡፡

 

በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት የካቲት 5 ቀን 2017 ዓ.ም የመተግበሪያዎቹ ሥራ ለማስጀመር በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሔኖክ ከበደ ባደረጉት ንግግር፣ “ወደ ሥራ ከሚገቡት ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነው ንብ አምበር ፔይ በንግድ ሥራ ላይ ለተሰማሩ የባንካችን ደንበኞች ለሚሰጡት አገልግሎት ከደንበኞቻቸው የሚከፈሉ ክፍያዎችን በቀላሉ በአስተማማኝ መንገድ በመተግበር፤ ክፍያን ከመቀበያነት በተጨማሪ ደንበኞች የንግድ እንቅስቃሴያቸውን በቀላሉ በእጅ ስልካቸው የሚከታተሉበትን መንገድ ተግባራዊ አድርጓል” ብለዋል።

 

ሁለተኛው ወደ ሥራ የሚገባው ፕሮዳክት ንብ ፔይስትሪም የተሰኘው የአገልግሎት መተግበሪያ ሲሆን፤ በበይነ መረብ የሚደረጉ ግብይቶችን ለማቀላጠፍ ታስቦ የተተገበረ ሲሆን ይህን መተግበሪያ በመጠቀም የንግዱ ማኅበረሰብ ለሚሰጧቸው አገልግሎቶች ክፍያቸውን በኦንላይን መቀበል የሚያስችላቸው መሆኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አስረድተዋል፡፡

 

ወደ ሥራ እየገባ ያለዉ ንብ አምበር ፔይ ለንግዱ ማኅበረሰብ ካቀረባቸው አራት የገንዘብ መቀበያ ዘዴዎች በተጨማሪ፤ መተግበሪያው ከአንድ በላይ የሽያጭ ሠራተኞች ላሏቸው የንግድ ተቋማትና ድርጅቶች ለሽያጭ ሠራተኞቹ በሚሰጥ የሞባይል መተግበሪያ ከአንድ ቋት ገንዘብ እንዲቀበሉ የሚያስችል በመሆኑ ከአንድ በላይ የሽያጭ ሠራተኞች በሚሰማሩባቸው የንግድ ቦታዎች  ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል፡፡

 

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ለትግበራ ያበቃቸው የዲጂታል ፕሮዳክቶች ዘመኑ የሚፈልገውን በተገቢው መንገድ በመረዳት፤ የደንበኞቻችን ምቾትና የሥራ ጥራት በዲጅታል ሥርዓት ለመለወጥ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች ከማሳየት ባሻገር በባንኩ የውስጥ አቅም በሚሠሩ የቴክኖሎጂ ሥራዎች ፍሬያማ ጉዞ መጀመሩን የሚያሳዩ እንደሆኑ አቶ ሔኖክ ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይም ባንኩ ጥረቱን አጠናክሮ፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እየተከታተለ ሥራ ላይ ማዋሉን እንደሚቀጥል በሥነ ሥርአቱ ላይ ተገልጿል፡፡

 

 

<p> <b>  <span style="color: #8B5E3C;">Nib International</span>   <span style="background: linear-gradient(to right, #8B5E3C, #FFA500); -webkit-background-clip: text; color: transparent; font-weight: bold;">     Bank   </span></b> </p>

Nib International Bank

Committed To Services Excellence

Share this post with

You May Also like

Reports

Jobs