Internet Banking
Internet Banking

ከባንኩ ከፍተኛ ባለ አክሲዮኖች ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ::

የባንኩ ከፍተኛ ባለድርሻ ከሆኑ ባለ አክሲዮኖች ጋር በባንኩ ወቅታዊ ሁኔታና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ዛሬ ምክክር  ተካሂዷል፡፡

 

በምክክር መድረኩ፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ሺሰማ ሸዋነካ እና የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር እመቤት መለሰ ባንኩ ያለበት ወቅታዊ ሁኔታና በቀጣይ መደረግ ያለባቸውን የመፍትሄ አቅጣጫዎች በመጠቆም የተዘጋጀውን መረጃ በዝርዘር አቅርበዋል፡፡ በቀረበው መረጃ ላይም ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡

 

በውይይቱም ባንኩ የነበረበትን አስቸጋሪ ጊዜ አልፎ አሁን ያለበትን ትክክለኛ መስመር ላይ እንዲመጣ ላደረጉ ለዳይሬክተሮች ቦርድ እና ለማኔጅመንት አባላት፣ ባለ አክሲዮኖች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

 

በቀጣይም ሁሉም ባለድርሻ የሚጠበቅበትን ሚና እንዲጫወትና ግዴታውን እንዲወጣ እንዲሁም ባንኩን  ወደ ተሻለ ከፍታ ማድረስ እንደሚገባ በመስማማት የዕለቱ የምክክር መድረክ ተጠናቅቋል፡፡

 

በምክክር መድረኩ ላይ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና የማኔጅመንት አባላት የተሳተፉ ሲሆን፤ መሰል መድረኮች ከዚህ በፊትም እንደተካሄዱ ይታወሳል፡፡

 

NIB BANK

NIB BANK

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs