ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ 1447ኛውን የረመዷን ፆም ምክንያት በማድረግ የገቢ ምንጫቸው አነስተኛ ለሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ምግብ ነክ ቁሳቁሶችን ዛሬ የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት በመገኘት ድጋፍ አደረገ፡፡
በመርሃ-ግበሩ ላይ የተገኙት የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ዋና ሥራ-አስኪያጅ ወ/ሮ ሀናን መሐመድ ባደረጉት ንግግር፤ የረመዷን ወር በባህሪው ሰዎች የሚደጋገፉበት፣ ያለው ለሌለው የሚያካፍልበት፣ የሚተሳሰቡበት እና የሀይማኖቱ ተከታዮች በጎ ሥራ በመሥራት ፈጣሪያቸውን የሚያከብሩበትና የሚያመሰግኑበት ወቅት እንደሆነ ጠቅሰው፤ ባንኩ ለፈጸመው ድጋፍ ከፍ ያለ ምሥጋና በተረጂዎች ስም አቅርበዋል፡፡
ባንኩ የረመዷን የጾም ወርን አስመልክቶ በቀጣይም በተለያዩ ዲስትሪክት ጽ/ቤቶች አማካኝነት ተመሳሳይ የድጋፍ ሥራዎችን እንደሚያከናውን ተጠቁሟል፡፡


ረመዷን ሙባረክ!!
አስር አመታት በሃላል አገልግሎት!



