Internet Banking
Internet Banking

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የ1447ኛው ዓመተ ሂጅራ የረመዷን የፆም ወርን አስመልክቶ እያደረገ የሚገኘውን የበጎ አድራጎት ተግባር አጠናክሮ ቀጥሏል።

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የ1447ኛው ዓመተ ሂጅራ የረመዷን የፆም ወርን አስመልክቶ እያደረገ የሚገኘው የበጎ አድራጎት ተግባር በጅማናና በአዲስ አበባ ከተሞች ተጠናክሮ ቀጥሏል።

 

በመርሃ ግብሩ ገቢያቸው አነስተኛ ለሆነ የማኅበረሰብ ክፍሎች የተለያዩ  የምግብ ነክ ቁሳቁሶች ድጋፍ የተደረገ ሲሆን በተለምዶ በአዲስ አበባ ጳውሎስ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው ከሲር ለና የበጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር ተከናውኗል። በተመሳሳይ በጅማ ከተማም ከኤርማታ መንቲና ቀበሌ አስተዳደር ለተመረጡ የማኅበረሠብ ክፍሎች ድጋፍ ተደርጓል።

 

ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖችም በባንኩ ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው ባንኩ ዕቅዱ የተሳካ እንዲሆንለት በዱዓና በምስጋና ምኞታቸውን ገልጸው መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

 

ረመዷን ሙባረክ!

አስር አመታት በሃላል አገልግሎት!

ይሠሯል ከልብ እንደ ንብ!

 

Picture of <p> <b>  <span style="color: #8B5E3C;">Nib International</span>   <span style="background: linear-gradient(to right, #8B5E3C, #FFA500); -webkit-background-clip: text; color: transparent; font-weight: bold;">     Bank   </span></b> </p>

Nib International Bank

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs