N
NIB Assistant
Online
 
Internet Banking
Internet Banking

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት በተካሄደው የመግባቢያ ስምምነት የፊርማ ሥነ ሥርዓት መርሐ ግብር ላይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የባንኩ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደ፣ ስምምነቱ ባንኩ ሥራ ላይ ባዋለው የሦስት ዓመት የስትራተጂ ዕቅድ እና የአምስት ዓመት ፍኖተ ካርታ ትኩረት ሰጥቶ ለመስራት ካቀዳቸው ዓበይት ጉዳዮች አንዱ ከሌሎች ተቋማት ጋር በአጋርነት አብሮ ለመስራት መሠል ሥምምነቶችን መፈፀም እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ሥምምነቱ ባንካችን ከኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ጋርም በዚሁ አግባብ ለመሥራት የሚያስችለው እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

በመግባቢያ ስምምነት የፊርማ ሥነ ሥርዓት መርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው ፊርማቸውን ያኖሩት የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኮ/ል ሸጋው ሙሉጌታ በበኩላቸው ከንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ጋር በጋራ ለመሥራት በመስማማታቸው ደስተኛ መሆናቸውን በተቋማቸው ሥም የገለጹ ሲሆን በቀጣይም የግሩፑ እህት ኩባንያዎችንም ከባንኩ ጋር በጋራ የሚሠሩበትን ሁኔታዎች የማመቻቸት ሥራዎች ይሠራሉ ብለዋል፡፡

***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!

Picture of <p> <b>  <span style="color: #8B5E3C;">Nib International</span>   <span style="background: linear-gradient(to right, #8B5E3C, #FFA500); -webkit-background-clip: text; color: transparent; font-weight: bold;">     Bank   </span></b> </p>

Nib International Bank

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs