በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት በተካሄደው የመግባቢያ ስምምነት መርሐ ግብር ላይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የባንኩ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደ፣ ስምምነቱ ባንኩ በካፒታል ገበያ ውስጥ ሊኖረው የሚችለውን እንቅስቃሴ ለማሳደግና ተወዳዳሪ ለመሆን ትልቅ አቅም የሚፈጥር በመሆኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ ይገባል ብለዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው ፊርማ ያኖሩት የሲቢኢ ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ በበኩላቸው ከንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ጋር በአጋርነት ለመሥራት በመስማማታችን ደስተኛ መሆናችንን እየገልጽን በእኛ በኩልም የሚፈለገውን እሴት በማከል በፍጥነት ወደ ሥራ እንገባለን ብለዋል፡፡
በፊርማ ሥነ ሥርዓት መርሐ ግብሩ ላይ የሁለቱም ባንኮች የማኔጅመንት አካላት ተሳትፈዋል፡፡