N
NIB Assistant
Online
 
Internet Banking
Internet Banking

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በአዳማ ከተማ ለሚገኙና ገቢያቸው አነስተኛ ለሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች ለትንሣኤ በዓል መዋያ ድጋፍ አደረገ።

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በአዳማ ከተማ ለሚኖሩና ገቢያቸው አነስተኛ ለሆነ  የማኅበረሰብ ክፍሎች የትንሣኤ በዓል መዋያ ድጋፍ ማድረግ ጀመረ።

መርሐ ግብሩ በአዳማ ከተማ በተከናወነበት ወቅት የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ተገኝተው አባታዊ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በድጋፍ አሰጣጥ መርሐ-ግብሩ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶች እና የባንካችን አዳማ ዲስትሪክት ኃላፊዎች ለተመረጡና ድጋፍ ለሚፈልጉ የህብረተሠብ ክፍሎች ለበዓል መዋያ የሚያገለግሉ የተለያዩ  ምግብ ነክ ቁሳቁሶችን አበርክተዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖችም ባንኩ ላደረገላቸው የቁሳቁስ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

ባንኩ የጀመረው የትንሳኤ በዓል  ማኅበራዊ ኀላፊነት የመወጣት ተግባር በተለያዩ አካባቢዎችም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።

Picture of <p> <b>  <span style="color: #8B5E3C;">Nib International</span>   <span style="background: linear-gradient(to right, #8B5E3C, #FFA500); -webkit-background-clip: text; color: transparent; font-weight: bold;">     Bank   </span></b> </p>

Nib International Bank

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs