N
NIB Assistant
Online
 
Internet Banking
Internet Banking

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በሐዋሳ ከተማ ለሚገኙና ገቢያቸው አነስተኛ ለሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች የትንሣኤ በዓል መዋያ  ድጋፍ አደረገ።

ባንኩ በሐዋሳ ከተማ ለሚኖሩና ገቢያቸው አነስተኛ ለሆነ  የማኅበረሰብ ክፍሎች የትንሣኤ በዓል መዋያ ድጋፍ በሐዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በመገኘት ድጋፍ አድርጓል።

በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሊ/ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ፣ የሀዋሳ ደ/ም/ቅ/ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪ እንዲሁም በርካታ የሀይማኖት አባቶች እና የባንኩ አመራሮች በተገኙበት ድጋፍ ተደርጓል።

በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ዮሴፍም ባንኩ ላደረገው ድጋፍ በቤተክርስቲያኗ ስም ምስጋና አቅርበው ተቋማት ተባብረው አቅመ ደካሞችን ቢያግዙ ድህነት ከሀገራችን እንደሚቀንስ ገልጸው ድሆችን በመርዳት ወገኖቻችንን እናስብ በማለት አሳስበው ባንኩ ላዘጋጀው የበዓል መዋያ ስጦታ ምስጋና አቅርበዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖችም ባንኩ ላደረገላቸው የቁሳቁስ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

ባንኩ የጀመረው የትንሳኤ በዓል  ማኅበራዊ ኀላፊነት የመወጣት ተግባር በተለያዩ አካባቢዎችም አሁንም በሌሎች አካባቢቢዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።

 

Picture of <p> <b>  <span style="color: #8B5E3C;">Nib International</span>   <span style="background: linear-gradient(to right, #8B5E3C, #FFA500); -webkit-background-clip: text; color: transparent; font-weight: bold;">     Bank   </span></b> </p>

Nib International Bank

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs