ታታሪው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተደራሽነቱን በማስፋት በቶሞካ ካፌ የንብ ኢ-ብር የዲጂታል ክፍያ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡
ደንበኞች ከመስከረም 14 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት በቶሞካ ካፌ ተጠቅመው በንብ ኢ-ብር ክፍያቸውን ሲፈጽሙ ትርጉም ያለው ቅናሽ እንደሚያገኙ ከባንኩ የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ቀደም ሲል ከነበሩት የዲጂታል ክፍያ አማራጮች በተጨማሪ ንብ ኢ-ብርን ሥራ ላይ በማዋል ተደራሽነቱን አስመስክሯል፡፡
ባንኩ፣ ከንብ ኢብር በተጨማሪ ከቴሌ ብርና ከጉዞ ጎ ጋር አብሮ በመሆን የዲጂታል ክፍያ አገልግሎቶችን ተግባራዊ በማድረግ ደንበኞች እንዲጠቀሙ ያደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ
ይሠሯል ከልብ እንደ ንብ!