Internet Banking
Internet Banking

የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የ25ኛ አመት የብር ኢዩቤልዩ በዓል ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት ተካሔደ።

ባንኩ ግንቦት 19 ቀን 1991 ዓ.ም የንግድ ፈቃድ ያገኘበትን ቀን (May 26) ምክንያት በማድረግ የብር ኢዩቤልዩ በዓሉን የመጀመሪያው በሆነው ”ሾላ ቅርንጫፍ” በተለያዩ ሥነ-ሥርዓቶች እያከበረ ይገኛል፡፡

 

በሥነ-ሥርዓቱ የተገኙት የባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድ ዋና ሊቀመንበር አቶ ሺሰማ ሸዋነካ እና አዲሷ ዋና ሥራ አስፈጻሚ እመቤት መለሰ(ዶ/ር) ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

 

በዚህም አቶ ሺሰማ ባንኩ እያከበረው በሚገኘው የብር ኢዩቤልዩ በዓል ውስጥ ጉልህ አስተዋጽኦ የነበራችሁ የሥራ ሀላፊዎች፣ ባለድርሻ አካላትና ደንበኞች እንዲሁም የባንኩ ማሕበረሰብ ”እንኳን አደረሳችሁ፤ እንኳን ደስ አላችሁ” ብለዋል።

 

ዶክተር እመቤት በበኩላቸው ”ባንኩ በበርካታ ሁኔታዎች ውስጥ እያለፈ በሚገኝበት በዚህ ወቅት በተለየ ሀላፊነት በመቀላቀሌ ደስተኛ ነኝ” ያሉ ሲሆን አሁንም ባንኩ ”በአዲስ መንፈስ ለላቀ ከፍታ” በሚል መርህ የተነሳለትን ዓላማ በማገዝ ሀገራዊ እና ተቋማዊ ተልዕኮዎቹን እንዲያሳካ ርብርብ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

 

ለዚህ ትልቅ ተነሳሽነትን የሚፈጥረውና ዛሬ የተበሰረው የባንኩ የ25ኛ ዓመት የብር ኢዩቤልዩ በዓል በተለያዩ ጊዜያት እያደጉ በሚሔዱ መርሐግብሮች ለቀጣይ ጥቂት ወራት እየተከበረ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!

NIB BANK

NIB BANK

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs