Internet Banking
Internet Banking

የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ የባንኩን የተከፈለ ካፒታል ወደ 20 ቢሊዮን ለማሳደግ ውሳኔ አሳለፈ።

የባንኩ 20ኛ የባለአክሲዮኖች አስቸኳይ ጉባኤውን ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ በተካሔደበት ወቅት ነው ይህ የተወሰነው።

የባንኩ አዲሱ የዲሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ሺሰማ ሸዋነካ ባደረጉት ንግግር ንብ ኢንተርናሽናል ባንክን ወደቀድሞ ከፍታው ለመመለስና ላቅ ወዳለ ደረጃ ለመድረስ በሚያስችለው ጉዞ ላይ መሆኑን ገልፀዋል።

”ንብ ባንክ በበርካታ ደንበኞች በተለይም በንግዱ ማህበረሰብ ዘንድ ተወዳጅ ባንክ ነው” ያሉት ሊቀመንበሩ ባለአክሲዮኖች ከምንጊዜውም በበለጠ ድጋፋቸውን እንዲያረጋግጡለት ጠይቀዋል።

የጉባኤው ተሳታፊ ባለአክሲዮኖችም አዲሱ ቦርድ ወደሥራ ከገባበት አጭር ጊዜ አኳያ ጥሩ ውጤት ለማስመስገብ የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ መሆኑን መገንዘባቸውን በዚህም ከጎኑ እንደሚቆሙ ገልፀዋል።

ከጉባኤው አጀንዳዎች መካከል አንዱ የነበረው የትርፍ ድርሻን በተመለከተም እ.አ.አ በ2022 በተገኘው ያልተወሰነበት የትርፍ ድርሻ ክፍፍል ላይ ውይይት በማድረግም ገንዘቡ ለባንኩ ካፒታል ማሳደጊያነት እንዲውል የባለአክሲዮኖች ጉባኤው በአብላጫ ድምፅ ወስኗል።

በባንኩ 18ኛው አስቸኳይ ጉባኤ የተወሰነውን የካፒታል ማሳደጊያ ጊዜ እንዲሻሻል በተደረገው ውይይትም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ተጠናቆ እንዲከፈል ተወስኗል።

NIB BANK

NIB BANK

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs