በውይይቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ በባንኩ ተፈጥሮ የነበረውን የአገልግሎት መቆራረጥ በማስተካከል ባንኩንም ሆነ ደንበኞቹን ለመካስ የሚያስችል እንቅስቃሴ መጀመሩን ተናግረዋል።
በዚህም ከጥሬ ገንዘብ እጥረት ጋር ተያይዘው የተስተዋሉ ክፍተቶችን በማረም አሁን ባንኩ ”በአዲስ መንፈስ ለላቀ ከፍታ” በሚል መርህ ለችግሮቹ ፈጣን መፍትሔ እየሰጠ ይገኛል ብለዋል።
ደንበኞች አሁን ማነኛውም የRTGS፣ የቼክ እና የጥሬ ገንዘብ ክፍያ አፈጻጸም ችግር እንደማያጋጥማቸውም ገልፀዋል።
ዶክተር እመቤት በሆሳዕና እና አካባቢው የባንኩ የረጅም ጊዜ ደንበኛ በመሆን አጋርነታቸውን ላሳዩ ደንበኞች ምሥጋና አቅርበዋል።
በውይይቱ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላትም አሁን የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ በመደገፍ አብረው እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
መረጃዎቻችንን ለሌሎች ስለሚያጋሩ እናመሰግናለን!
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!