”በአዲስ መንፈስ ለላቀ ከፍታ” በሚል መሪ ሃሳብ የለውጥ እንቅስቃሴውን አጠናክሮ በቀጠለው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አዲሷ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር እመቤት በሆሳዕና ዲስትሪክት ጽህፈት ቤትና በስሩ ከሚገኙ የቅርንጫፍ ሠራተኞች ጋር በሆሳዕና ከተማ በተዘጋጀ መድረክ ተዋውቀዋል።
በትውውቅ ፕሮግራሙ ከዋና ሥራ አስፈጻሚዋ በተጨማሪ የባንኩ የደንበኞች እና ቅርንጫፍ ባንኪንግ ዋና መኮንን አቶ ግርማ ፈቀደ የተገኙ ሲሆን ከፈንረጆቹ ጁን 01 2024 እስከ ሴፕቴምበር 30 2024 ድረስ ባሉት 120 ቀናት ውስጥ የሚከናወኑ ተግባራትን የሚገልጽ እቅድ አቅርበው ውይይት ተካሂዶበታል።
በውይይቱ በዲስትሪክቱ ስር የሚገኙ ሠራተኞች ለእቅዱ ተፈጻሚነት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለመወጣት ጠንክረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
በቦርዱ፣ በማኔጅመንቱ እና በሠራተኛው ርብርብ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተገኘው ውጤት ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ያሳሰቡት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ የታለመውን እቅድ ማሳካት የሁሉም ሀላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል።
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!