የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የደንበኞች ቀን በወጣለት መርሐ ግብር መሠረት በሁሉም የባንኩ ቅርንጫፎች በመካሄድ ላይ ነው፡፡
ዛሬ ሰኞ ግንቦት 21 ቀን 2015 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ የተጀመረው የደንበኞች ቀን፣ ደንበኞችን ማዕከል ባደረጉ የተለያዩ አገልግሎቶች እስከ ሰኔ 23 ቀን 2015 ዓ.ም ይቆያል፡፡
በዚህም የትግበራ ጊዜ ከደንበኞች ጋር ያለውን ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ ማሳደግ፣ የቁጠባ ባህል እንዲዳብር ተገቢውን ሁሉ በማድረግ ነባር ደንበኞችን በማርካት፣ አዳዲስ ደንበኞች ደግሞ ባንኩን እንዲቀላቀሉ በማድረግ ውጤታማ ሥራ ለመሥራት ታስቦ የተዘጋጀ መርሐ ግብር ነው፡፡
የባንኩ ቅርንጫፎች ቀድሞ ከነበረው በበለጠ ደረጃ ወደ ደንበኞች በመቅረብ ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት መልካም የሥራ ግንኙነት እንዲፈጠር ይደረጋል፡፡ በዚህ መርሐ ግብር የአገልግሎት አሰጣጡን ይበልጥ በማሳደግ የባንኩን የገጽታ ግንባታ ሥራ ከፍ ለማድረግ ከመሥራቱ ጎን ለጎን ደንበኞች የሚመሰገኑበት ጊዜም ይሆናል፡፡
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!