የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የ2022/2023 የሶስተኛው ሩብ ዓመትና የዘጠኝ ወር የሥራ አፈጻጸም ስብሰባ ማክሰኞ ሚያዚያ 24 ቀን 2015 ዓ.ም በአራት ኪሎ የባንኩ ሕንጻ መሰብሰቢያ አዳራሽ እና ቅዳሜ ሚያዚያ 28 ቀን 2015 ዓ.ም በዋናው መሥሪያ ቤት አዳራሽ ተካሄደ፡፡
የባንኩ የማኔጅመንት እንዲሁም የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት በተሳተፉበት በዚህ ስብሰባ፤ በሶስተኛው ሩብ ዓመትና ባለፉት ዘጠኝ ወራት ባንኩ ያከናወናቸው ሥራዎች ተገምግመው ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ በማስቀጠል፤ ክፍተት የታየባቸውን ደግሞ በማረም ባንኩን ወደ ተሻለ የአፈጻጸም ደረጃ ለማሳደግ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
ባንኩ በበጀት ዓመቱ በፋይናንሱ ዘርፍ በዓለም ላይ የተከሰቱትን በርካታ ተግዳሮቶችን በመቋቋም ሐብት ከማሰባሰብ፣ ደንበኛን ከማፍራትና ከሌሎች መመዘኛዎች አንጻር በአፈጻጸሙ ዙሪያ ግምገማ ተካሂዶ ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ውጤት እንዳስመዘገበ ተገልጿል፡፡
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በቅርቡ የተከለሰውን ስትራቴጂክ (መሪ) እቅድ በመተግበር ላይ ሲሆን፤ አሁን የተገኘውን ውጤት መሠረት በማድረግ በቀጣይ ጊዜያትም ይበልጥ ጠንክሮ ሠርቶ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ አቅጣጫ በማስቀመጥ ስብሰባው ተጠናቋል፡፡
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!