በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ እና በፈርስት ኮንሰልት (ብሪጅስ ፕሮግራም-ኢትዮጵያ) መካከል ለማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ፋይናንስ ለማቅረብ የሚያስችል የሁለትዮሽ ስምምነት መስከረም 5 ቀን 2015 ዓ.ም በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ተፈረመ፡፡
ፊርማውን የፈረሙት በባንኩ በኩል የባንካችን ፕሬዚዳንት አቶ ገነነ ሩጋ ሲሆኑ በፈርስት ኮንሰልት (ብሪጅስ ፕሮግራም-ኢትዮጵያ) በኩል ደግሞ የቡድን አስተባባሪው አቶ ሔኖክ ጠና ናቸው፡፡
የስምምነቱ ዓላማ በጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ዘርፍ ለተሰማሩ ከስድስት መቶ ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ሲሆን፤ እነዚህም ድርጅቶች የብድር አገልግሎት በተመረጡ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት በኩል እንዲያገኙ እንደሚደረግ ታውቋል፡፡