Internet Banking
Internet Banking

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አዳዲስ ሹመቶችን ሰጠ

በአዲስ መንፈስ፣ ለላቀ ከፍታ! በሚል መሪ ቃል በመታጀብ በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ አዳዲስ ሹመቶችን ሰጠ፡፡

 

በቅርቡ የተወሰኑ ቺፎች፣ ምክትል ቺፎች፣ ምክትል ፕሬዚዳንቶችና የመምሪያ ዳይሬክተሮች ከኃላፊነታቸው የተነሱ ሲሆን፤ በምትካቸውም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተሹመዋል፡፡ በዚህም መሠረት፦ አቶ ግርማ ፈቀደ – ቺፍ ደንበኞችና ቅርንጫፍ ባንኪንግ ኦፊሰር፣ አቶ ሳምሶን አምዲሳ – ቺፍ ፋይናንስና ፋሲሊቲ ኦፊሰር፣ አቶ በላይ ጎርፉ – ምክትል ቺፍ ስትራቴጂና ትራንስፎርሜሽን ኦፊሰር፣ ወይዘሮ ሐረገወይን አምሳለ – ምክትል ቺፍ ዓለም አቀፍ ባንኪንግ ኦፊሰር፣ አቶ ዘውዱ ሐኪሙ – ምክትል ቺፍ ሒዩማን ካፒታል ኦፊሰር እና አቶ ነጻነት ይርጋ ምክትል ቺፍ ክሬዲት ኦፊሰር ናቸው፡፡

 

በተያያዘም፣ ዛሬ ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም አዳዲስ የሥራ ኃላፊዎች ከቀሪዎቹ ነባር የማኔጅመንት አባላት ጋር በዋናው መሥሪያ ቤት የትውውቅ መድረክ ተካሂዷል፡፡ በዚህም ሥነ ሥርአት ላይ ባንኩን የተቀላቀሉት አዲሶቹ የማኔጅመንት አባላት፤ ቀድሞ ይሠሩበት ከነበረው ተቋም በተሻለ ደረጃ ለማገልገልና ባንኩ አሁን ካለበት ችግር እንዲላቀቅ ከአቅም በላይ ለማገልገል እንደተዘጋጁ አረጋግጠዋል፡፡ “ምቹና ከስጋት ነጻ ከሆነ ሥራ ላይ ወጥቶ ተግዳሮት ወዳለበት የሥራ ከባቢን መቀላቀል እጅግ ተፈላጊና መልካም አጋጣሚ ነው፡፡” ብለዋል፡፡

 

የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ባለአክስዮኖች፣ ታኅሣስ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄዱት 24 መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የተመረጠው አስራ ሁለት አባላት ያሉት አዳዲስ የዲሬክተሮች ቦርድ ከጥር 27 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሥራ በመግባት፤ ባንኩ ያጋጠሙትን ችግሮች ለመፍታት የዘጠና ቀናት ዕቅድ በማዘጋጀት በርካታ ሥራዎችን ሲያከናውን መቆየቱ ይታወቃል፡፡

 

በዚህ ጊዜ ውስጥ ከተሠሩት ሥራዎች መካከል እመቤት መለሰ (ዶ.ር)ን የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ በመሰየም ባንኩ ካጋጠሙት ተግዳሮቶች ለማውጣት ያላሰለሰ ጥረት በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡

NIB BANK

NIB BANK

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs