የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ዶ/ር እመቤት መለሰ ባንኩ ባለፉት ጥቂት ወራት አጋጥሞት ከነበረው ጊዜያዊ ችግር ለመላቀቅ በትኩረት የተንቀሳቀሰ ሲሆን ባሁኑ ወቅትም ንብ ባንክ በሚታወቅባቸው አገልግሎቶች ደንበኞቹ ጋር እየደረሰ መሆኑን በውይይቱ ተናግረዋል።
“በአዲስ መንፈስ ለላቀ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል ወደ ስራ የገባው ባንኩ ቀድሞ ከሚታወቅባቸው አገልግሎቶቹ ልቆ ለመምጣት በከፍተኛ ጥረት ላይ እንደሚገኝ ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ተናግረዋል።
በደሴ ከተማና በአካባቢው በሌሎች ከተሞችም ተደራሽነትን ለማስፋት የታቀደ ሲሆን ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት የሚሰጥባቸውን ቅርንጫፎች ወደ ስራ ለማስገባትና የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቱ የተቀላጠፈ እንዲሆን እየተደረገ ነውም ብለዋል።
በመሆኑም ደንበኞች ባንኩ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ የገባ መሆኑን ተገንዝበው በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ ቀርቧል።
ዋና ስራ አስፈጻሚዋ ዶ/ር እመቤት መለሰን ጨምሮ የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች በተካተቱበት ውይይት በተለያየ የንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላት እና ደንበኞች ለባንኩ ያላቸውን ውግንና በተመለከተ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!