ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የላቀ አፈጻጸም በማስመዝገብ በታማኝ ግብር ከፋይነት የፕላቲንየም ሽልማት ተሸላሚ ሆነ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ.ም በተካሄደው የግብር ከፋዮች የእውቅናና የማበረታቻ ሽልማት ሥነ ሥርአት ላይ ተገኝተው ሽልማቱን፣ የባንካችን ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ መልካሙ ሰለሞን ከኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ክብርት ሣህለወርቅ ዘውዴ እጅ ተቀብለዋል፡፡
በዘንድሮው የእውቅናና የሽልማት ሥነ ሥርአት ላይ የቀረቡት 400 ግብር ከፋዮች ሲሆኑ፤ በዚህም መሠረት 40 የፕላቲንየም፣ 120 የወርቅና 240 የብር ደረጃ ተሸላሚዎች ሆነዋል፡፡
ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው ከሆነ፤ በ2011 ዓ.ም 163፣ በ2012 ዓ.ም 200፣ በ2013 ዓ.ም 300 እና በ2014 ዓ.ም 400 ግብር ከፋዮች ተመርጠው ለሽልማት በቅተዋል፡፡
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በተከታታይ ዓመታት በታማኝ ግብር ከፋይነት ሽልማት የወሰደና በአገሪቱ ካሉ የግል ባንኮች ተጠቃሽ ባንክ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ይሠሯል ከልብ እንደ ንብ!