Internet Banking
Internet Banking

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በሐዋሳ ዲስትሪክት ስር ከሚገኙ ዋና ዋና ባለድርሻ አካላትና ደንበኞች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

ባንካችን “በአዲስ መንፈስ ለላቀ” ከፍታ ብሎ የተነሳበትን አላማ ለማሳካት አሁንም ቁርጠኛ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ይገኛል፡፡

የዚህ አንዱ አካል የሆነው ባለድርሻ አካላትንና ደንበኞችን የማነጋገር እንዲሁም ዘላቂ የህዝብ ግንኙነት ሥራን የማጠናከር ጉዳይ በስፋት እየተከናወነ ነው፡፡

በባንካችን የደንበኞች እና ቅርንጫፍ ባንኪንግ ዋና መኮንን ግርማ ፈቀደ የተመራ ልዑክ በሐዋሳ ከተማ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትና ደንበኞች ጋር ውጤታማ ውይይት አድርጓል፡፡

በውይይቱም በተቋም ደረጃ አጋር የሆኑ አካላትና ደንበኞች ከባንኩ ጋር በተሻለ መልኩ አብሮ መሥራት ስለሚችሉበት ሁኔታ መክረዋል፡፡ ልዑኩ በሐዋሳ ቆይታው በአጋር አካላትና ደንበኞች የሥራ ማዕከላት በመገኘት ምልከታ አድርጓል፡፡

***

ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!

NIB BANK

NIB BANK

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs