ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ ከአዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር መሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማኅበር ጋር የኮር ባንኪንግ ሥራዎችን የሚያስተሳስር የሲስተም ትስስር (System Integration) የትግበራ ውል ስምምነት አቡዋሬ በሚገኘው የማኅበሩ ዋና መሥሪያ ቤት ህዳር 23 ቀን 2015 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተፈራረመ፡፡
የሲስተም ትስስር ትግበራው፣ የማኅበሩ አባላት ወርሃዊ የቁጠባ ሂሣባቸውንም ሆነ የብድር ክፍያቸውን በባንኩ በሚገኘው የማኅበሩ ሂሣብ ሲያስገቡ በፍጥነት (Real Time) አዋጭ ወደሚገኘው ሂሣባቸው ይተላለፋል፡፡ በተጨማሪም የባንኩንና የኅብረት ሥራ ማኅበሩን ሂሣብ ለማወራረድ የሰው ጣልቃ ገብነት በሌለበት ማከናወን የሚያስችል ሲሆን፣ ይህም ለሌሎች የዲጂታልና ኤሌክትሮኒክ ማበልጸግ ሥራዎች በር መክፈቱንና አመቺነትን የፈጠረ መሆኑም በፊርማ ሥነ ሥርአቱ ላይ ተገልጿል፡፡
የመግባቢያ ስምምነቱን፣ አቶ ልዑልሰገድ ንጉሤ የባንካችን የስትራቴጂና ትራንስፎርሜሽን ምክትል ፕሬዚዳንት እና አቶ ሰለሞን ወሌ የአዋጭ የኮር ባንኪንግና ሶፍትዌር ማስፋፊያ ኃላፊ ፈርመዋል፡፡
ይሠሯል ከልብ እንደ ንብ!
ዌብ ሳይት፡ www.nibbanksc.com
የፌስቡክ ገፃችን፡ https://bit.ly/3C33uM1
የኢንስታግራም ገፃችን፡ https://bit.ly/3p8OUuy
ሊንክዲን፡ https://bit.ly/3bJUhgG
የቴሌግራም ቻናላችችንን ለመቀላቀል፡ https://bit.ly/3SBzNYd
የሶሻል ሚዲያ ገፆቻችንን Like, Follow እና Share ማድረግዎን አይርሱ!
#nib #nibbank #budget #friday #nibbankofficialpage #banksinethiopia #fintech #bank #finance #ethiopia #ethiopian