ንቅናቄው እስከ አረፋ በዓል ዋዜማ በተለያዩ ከተሞችና ቅርንጫፎች እየተስፋፋ ይከናወናል። በዚህም የነባር ደንበኞች የተቀማጭ ገንዘብ መጠንን የማንቃት፣ አዳዲስ አካውንቶችን የማፍራት እና የገፅታ ግንባታ ሥራ የማጎልበት ተግባራት ይከናወናሉ።
”በአዲስ መንፈስ ለላቀ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል የለውጥ እንቅስቃሴውን አጠናክሮ የቀጠለው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በአዳዲስ የሥራ ሃላፊዎችና አሰራሮች ታግዞ ይበልጥ ወደ ደንበኞቹ እየቀረበ ይገኛል።
የማርኬቲንግ ንቅናቄውን እንቅስቃሴ በከፊል የሚያሳዩ ምስሎችን በዚህ ማስፈንጠሪያ https://www.nibbanksc.com/gallery/ መመልከት ይችላሉ፡፡
ኢድ ሙባረክ!
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!