Internet Banking
Internet Banking

”በአዲሱ የሥራ ዘመን እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደ ስኬት እንጓዛለን”-የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር እመቤት መለሰ።

ባንኩ አዲሱ የ2024/25 የሥራ ዘመንን በማስመልከት ሁሉም የዲስትሪክትና መምሪያ ዳይሬክተሮች እንዲሁም የማኔጅመንት እና የቦርድ አባላት የተገኙበት የማነቃቂያ ፕሮግራም አካሂዷል።

የባንኩ መላ ማሕበረሰብ ያለፈውን በጀት ዓመት ክፍተቶች በቁጭት ብቻ ሳይሆን በተነቃቃ መንፈስ ማጠናቀቁ ትልቅ ዋጋ እንዳለው ዋና ሥራ አስፈፃሚዋ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ገልጸዋል።

እስካሁን በበርካታ መስኮች እርማት አድርገናል ያሉት ዶክተር እመቤት፤ የአሰራር ክፍተቶች የፈጠሩብንን እዳዎች እያወራረድን ብንቆይም በጀት አመቱ ሳይጠናቀቅ ያከናወንናቸው ተግባራት በቀጣይ አመት ከነዚህ ችግሮች ሙሉ በሙሉ መላቀቅ ሁላችንም በተመሳሳይ ገፅ እንድንገኝ የሚያስችሉን ናቸውም ብለዋል። ንብ ባንክ በርካታ ጠንካራ ጎኖች እንዳሉት ያነሱት ዶክተር እመቤት ባንኩ በአጭር ጊዜ ትርፋማ እንደሚሆንም አመላካች ነገሮች እንዳሉ ጠቁመዋል።

የባንኩ የደንበኞች እና ቅርንጫፍ ባንኪንግ ዋና መኮንን አቶ ግርማ ፈቀደ በመድረኩ የቀጣይ አመት የሥራ አቅጣጫን የተመለከተ ሰነድ በማቅረብ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህም ባንኩ በቀጣይ ላቅ ያለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ያስችለዋል የተባለለትን ፍኖተ ካርታ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።

ውይይቱን የመሩት የባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር ኢንጂነር ወንድሙ ተክሌ እና የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር እመቤት መለሰ ናቸው።

ተሳታፊዎችም በሰጡት አስተያየት የቀረበውን ሰነድ ተግባራዊ በማድረግ ባንኩን ወደፊት ማምጣት አለብን ብለዋል።
***

ይሠሯል ከልብ እንደ ንብ!

NIB BANK

NIB BANK

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs