ሰኔ 26 ቀን 2013 ዓ.ም
 
ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የቁጠባ ባህልን ማሳደግ ለባንካችንም ሆነ ለሀገራችን የሚሰጠው ከፍተኛ ጠቀሜታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ከሚሰጣቸው የባንክ አገልግሎቶች ጎን ለጎን አገልግሎቶቹን በስፋት ለሚጠቀሙ ደንበኞቹ በርካታ የማበረታቻ ሽልማቶችንም በሎተሪ ዕጣ መልክ ሲሸልም ቆይቷል፡፡ የማበረታቻ ሽልማቶቹን ከጊዜ ወደ ጊዜ በአይነት፣ በብዛትም ሆነ በጥራት እያሻሻለ ዕድለኞችን ተጠቃሚ ማድረጉን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡  

ሰኔ 25 ቀን 2013 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አዳራሽ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ ዕጣው በይፋ ወጣ:: ሉሲ የሴቶች የቁጠባ ሂሳብ ከታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ግንቦት 21 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በባንካችን የቆጠቡ እንስት ደንበኞችን ባለ ዕድል የሚያደርጉ አሸናፊ ዕጣዎች ተለይተው ታወቁ፡፡

በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አዳራሽ ሰኔ 25 ቀን 2013 ዓ.ም በወጣው ሉሲ የሴቶች የቁጠባ ሂሣብ መርሃ ግብር፤

የአንደኛ ዕጣ ዕጣ አሸናፊ ወደ ኬንያ ሞምባሳ ደርሶ መልስ የጉዞ ቲኬትና ለጥንዶች ለ3 ቀናት ቆይታ ሙሉ ወጪ

ሁለተኛ ዕጣ 2 ሶፋና 2 ቴሌቪዥን

ሶስተኛ ዕጣ 4 የሴቶች ጸጉር መሥሪያ ዕቃዎች

አራተኛ ዕጣ 2 ለ6 ወራት የሚቆይ የጂምናዝየም አገልግሎት ፓኬጅ

አምስተኛ ዕጣ 3 የአገር ባህል ቀሚስ

ስድስተኛ ዕጣ 5 የምግብ መፍጫ ማሽን

ሰባተኛ ዕጣ 5 ማይክሮ ዌቭ

ስምንተኛ ዕጣ ለሶስት ሰዎች የምግብ አዘገጃጀት ስልጠና

ዘጠነኛ ዕጣ 5 ዲጂታል የእንጀራ ምጣድ

 አስረኛ ዕጣ 10 የስፓ ፓኬጅ እና

አስራ አንደኛ ዕጣ 5 የምግብ ማብሰያና ማሞቂያ ፍሪጆች ለባለዕድለኞች ተዘጋጅተዋል፡፡

የሉሲ የሴቶች የቁጠባ ባለዕድለኞች በቅርቡ በባንኩ በሚዘጋጀው ደማቅ የርክክብ ሥነ ሥርአት ላይ ሽልማታቸውን ይረከባሉ፡፡ 

ከንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ጋር ለሚሠሩና  ገንዘባቸውን በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ለሚቆጥቡ ደንበኞች ሌላው የተዘጋጀው እንሸላለም (ይቆጥቡ ይሸለሙ) የሎተሪ መርሃ ግብር በቅርቡ ዕጣው የሚወጣ ሲሆን ለባለዕድለኞችም መለስተኛ የጭነት መኪና፣ ባጃጆች፣ የውኃ ፓምፖችና ስማርት የሞባይል ቀፎዎች ለመሸለም ባንካችን ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ

ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ! 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *