ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከጊዜ ወደ ጊዜ አሠራሩን በማዘመን እና የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት እንዲሁም ዘመን ባፈራቸው ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ ደንበኞቹንና አገልግሎት ፈላጊዎችን ለማርካት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ባንኩ፣ አገልግሎቶቹን ለደንበኞቹ ምቹና ቀልጣፋ ከማድረግ አኳያ የኢትዮ ቴሌኮም የባለ ገመድ ስልክ፣ የሞባይልና የብሮድ ባንድ ክፍያዎችን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቲኬት ክፍያ፣ ጉዞ-ጎ (የተለያዩ አየር መንገዶች የቲኬት ክፍያ)፣ የቀላል ትራንስፖርት ክፍያ፣  እንዲሁም የትምህርት ቤት ክፍያዎችን በፍጥነት መፈጸም የሚያስችል ዘመናዊ አሠራር ተግባራዊ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

በዚህም መሠረት፣ ባንካችን ይህን ጥረቱን አጠናክሮ በመቀጠል ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የባለ ገመድ፣ የሞባይል ስልክና የብሮድ ባንድ ክፍያን፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ከፍሎ ካሽ ጋር በመተባበር የአየር መንገዱ የቲኬት ክፍያን፤ ከጉዞ-ጎ (ሶልጌት ትራቭል ፒኤልሲ) ጋር በመተባበር የአስር አየር መንገዶች የጉዞ ቲኬት ክፍያን፤ ከፍሎ ካሽ (ዴላፎን ቴክኖሎጂስ) ጋር ለጊዜው የቀላል ትራንስፖርት በቀጣይም የተለያዩ ክፍያዎችን፤ እንዲሁም የትምህርት ቤቶች ክፍያን ማስፈጸም የሚያስችለውን አሠራር ዘርግቷል፡፡

ባንኩ በተለያዩ የንግድና የአገልግሎት ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የባንክ አገልግሎትን በማስፋፋት ሕዝባዊ መሠረቱንና የንግድ አጋርነቱን በማጠናከር ላይ እንደሚገኝ ከባንኩ የወጣው መረጃ ያመለክታል፡፡

በሌላ በኩል፣ ታታሪው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና መሥሪያ ቤቱን ሰንጋ ተራ አካባቢ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስኩል ኦፍ ኮሜርስ ፊት ለፊት ወዳስገነባው ሰማይ ጠቀስ ሕንጻ አዘዋውሮ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡

አዲሱ የባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት 4B+G+32 ሕንጻ ለአገሪቱም ሆነ ለመዲናይቱ አዲስ አበባ የገጽታ ግንባታና ውበት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ሲሆን በጣም ዘመናዊና ለሥራ ምቹ ሆኖ የተገነባ መሆኑም ከባንኩ ከተገኘው መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህ ሕንጻ ምናልባትም በአገራችን ኢትዮጵያ ሥራ የጀመረ የመጀመሪያው ሰማይ ጠቀስ ሕንጻ በመሆኑ ባንካችን በዚህ ረገድ ፈር ቀዳጅ ያደርገዋል፡፡

ሕንጻው የባንኩን መለያ ቀለም (ብራንድ) በጠበቀ መልኩና በተለየ የዲዛይን ጥበብ መገንባቱም ከሌሎች ተቋማት ሕንጻዎች ለየት ያደርገዋል፡፡ 

ባንኩ በአሁኑ ወቅት ከ380 በላይ ቅርንጫፎች እንዲሁም ከ7100 በላይ ሠራተኞች ያሉት ሲሆን ተቀማጭ ገንዘብ ከ39 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን፣ እንዲሁም የብድር መጠኑ 32 ቢሊዮን ብር፣ አጠቃላይ ሀብቱ ወደ 50 ቢሊዮን ብር መድረሱን እና በካፒታልም ረገድ ኢንዱስትሪው ውስጥ ካሉ ባንኮች በሁለተኛ ደረጃ የሚቀመጥ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ

ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *