ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በሆሳዕና ከተማ ያስገነባውን ሕንጻ የባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የተሇያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ጥር 23 ቀን 2012 ዓ.ም ተመረቀ፡፡ ካሇፉት አራት ዓመታት ጀምሮ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ግንባታቸው እየተከናወኑ ከሚገኙ የባንኩ የህንጻ ግንባታ ፕሮጀክቶች መካከል ተጠናቀው የተመረቁት በዱከምና ወልቂጤ የሚገኙት ሲሆኑ፤ በአዲስ አበባና በሀዋሳ ያለት ግንባታቸው እየተጠናቀቀ ይገኛል፡፡ በሆሳዕና የተገነባው ሕንፃ ደግሞ እነሆ ሇመመረቅ በቅቷል፡፡
ባንካችን ሕንጻውን ሇማስገንባት ሆሳዕና ከተማን የመረጠበት ዋነኛ ምክንያት በደቡብ ክልል ከሚገኙ ከብዙ ከተሞች ጋር ሇመገናኘት አመቺ በመሆኑ ይህንን ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ የሚሰጣት መልክዓ ምድራዊ አቀማመጧን ታሳቢ በማድረግ ነው፡፡
የግንባታው ይዞታ ቦታው ጠቅላላ ስፋት 587.8 ካሬ ሜትር ሲሆን፣ ሕንጻው በ431.81 ካሬ ሜትር ላይ አርፏል፡፡
ሕንጻው ከቅርንጫፍ ባንክ አገልግሎት በተጨማሪ ሱቆችን፣ የካፊቴሪያ አገልግሎት መስጫ፣ የእንግዳ ማረፊያዎችንና የስብሰባ አዳራሽን የሚያካትት ሲሆን በአካባቢው የሚገኙትን የባንካችንን ቅርንጫፎች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የሆነው የሆሳዕና ዲስትሪክት ቢሮም በሕንጻው ላይ ተከፍቷል፡፡
ከሆሳዕና ከተማ በተጨማሪ በሐዋሳ ከተማ ልዩ ስሙ ፒያሳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከፍታው ከመሬት በላይ ባሇ አስርና ባሇ አስራ ሁሇት ወሇል (2B+G+9 እና G+11) የሆኑ መንትያ ሕንጻዎችን የያዘ ሁሇገብ ሕንጻ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ ሕንጻው ባሇ ሁሇት ቤዝመንት ሲሆን የቦታው ስፋት 1,980 ካሬ ሜትር ነው፡፡
በዚሁ ክልል ጉራጌ ዞን፣ ወልቂጤ ከተማ የሚገኘውና በ594.38 ካሬ ሜትር ላይ የተገነባው (G+3) ሕንጻ ሲሆን ከሶስት ዓመት በፊት ተጠናቆ ሥራ ጀምሯል፡፡ በኦሮሚያ ክልል በዱከም ከተማ በ2,353 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተገነባው ባሇ አምስት ወሇል ዘመናዊ ሕንጻም ሥራ ከጀመረ ሁሇት ዓመት ሞልቶታል፡፡
በመዲናችን አዲስ አበባ የባንካችን ሁሇት ግዙፍ የግንባታ ፕሮጀክቶች የሚገኙባት ከተማ ስትሆን በተሇምዶ ‹‹ሰንጋ ተራ›› ተብሎ በሚጠራው ስፍራ የወደፊቱ የባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት ሕንጻ በ3682.4 ካሬ ሜትር ላይ የማጠናቀቂያ ሥራው እየተሠራ ይገኛል፡፡ ይህ ግዙፍ ሕንጻ በአጠቃላይ 37 ወሇል ያሇው ነው (አራት ቤዝመንት+ግራውንድ+32)፡፡
ሌላኛው ባንካችን በጨረታ አሸንፎ ወደ ባንኩ ንብረትነት ያዞረው አራት ኪሎ የሚገኘውና በ2,926 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው ከመሬት በላይ ባሇ 8 ወሇል (2B+G+7) ሕንጻ የግንባታ ሥራው በቅርቡ ይጠናቀቃል ተብሎ እየተጠበቀ ነው፡፡
ባንካችን እያከናወነ ያሇው ተግባር በግንባታው ዘርፉ ከሚኖረው በጎ አስተዋፅኦ ባሻገር በአገር ኢኮኖሚ ላይም የሚያሳድረው ተጽዕኖ እያደገ መሄዱን ያመላክታል፡፡ በተጨማሪም ይህ አካሄድ የባንኩን እሴት ግንባታ የተጠናከረ እንዲሆን ከማድረጉም በላይ ተወዳዳሪነቱንም በዘላቂነት ሇማስቀጠል የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡