N
NIB Assistant
Online
 
Internet Banking
Internet Banking

22ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በባንካችን ተከበረ

22ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ትውልድን በሥነ-ምግባር፤ ተቋምን በአሠራር!” በሚል መሪ ሃሳብ፤ ኀዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም የባንኩ ከፍተኛ እና መካከለኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በባንኩ ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ተከበረ፡፡

በዓሉን በንግግር የከፈቱት የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደ፣ በዓሉን አስመልክተው ባደረጉት ንግግር ባንካችን በከፍተኛ የለውጥ እንቅስቃሴ ላይ ሆኖ የአገልግሎት አሰጣጡን የበለጠ ቀልጣፋ ለማድረግ ከሚያከናውናቸው ጥረቶች ጎን ለጎን፤ ሠራተኞቹን በሥነ-ምግባር በማነጽና ተቋማዊ አሠራርን በማዘመን ሙስናን ለመታገል ተግቶ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

22ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ከሚከበርበት ዋና ዋና ዓላማዎች መካከል፤ የፀረ ሙስና ትግሉ ህዝባዊና ተቋማዊ መሰረት እንዲኖረው አሳታፊና አካታች ንቅናቄ ለማድረግ፣ በፀረ ሙስና ትግሉ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲመዘገብ ለማነቃቃት እንዲሁም የተቋማት መሪዎች ለፀረ ሙስና ትግሉ አርኣያና ግንባር ቀደም መሆናቸውን የሚያሳዩበት መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል፡፡

በመድረኩም በኮሚሽኑ የተዘጋጀ በድምጽ የተቀረጸ የውይይት መነሻ ሰነድ ለተሳታፊዎች ቀርቦ ውይይት ተካሄዷል፡፡ በመጨረሻም የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የሞሏቸውን የሀብት ማሳወቂያ የምዝገባ ሰነድ ለኮሚሸኑ ተወካዮች ርክክብ በማድረግ በዓሉ ተጠናቋል፡፡

***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!

 

Picture of <p> <b>  <span style="color: #8B5E3C;">Nib International</span>   <span style="background: linear-gradient(to right, #8B5E3C, #FFA500); -webkit-background-clip: text; color: transparent; font-weight: bold;">     Bank   </span></b> </p>

Nib International Bank

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs