N
NIB Assistant
Online
 
Internet Banking
Internet Banking

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መስጠት የጀመረበትን 10ኛ ዓመት አከበረ

የበዓሉን አከባበር አስመልክቶ ዛሬ ታኅሳስ 10 ቀን 2018 ዓ.ም በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት በተካሄደው መርሐ ግብር፤ የባንኩ የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ ሰብሳቢ፣ የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሺሰማ ሸዋነካ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ባንኩ በጠንካራ መሰረት ላይ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ይህንን ልዩ ክብረ በዓል ማክበር በመቻሉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡

የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሄኖክ ከበደ ባደረጉት ንግግር “ንብ ሃላል” አገልግሎትን እየሰጠ ባሳለፋቸው 10 ዓመታት፤ ከጎኑ ለነበሩ አካላት በሙሉ፤ በተለይም ለደንበኞች፤ ለባንኩ የቦርድ አመራሮች፣ ለሸሪዓ አማካሪ ቦርድ አባላት እና ለባንኩ ሠራተኞች የላቀ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ “እንኳን ለንብ ሃላል 10ኛ ዓመት አደረሳችሁ” በማለትም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡

የባንኩ የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር መሐመድ ዘይን ኑር ሁሴን በበኩላቸው፤ ባንኩ ንብ ሃላልን ወደ ሥራ ካስገባበት ጊዜ አንስቶ ሁሉም አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ የሸሪዓ ሕግጋትን ባሟላ መልኩ እየተሰጡ እንደሚገኙ አረጋግጠው፤ ይህን ለማድረግ ለተጉ የባንኩ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ከፍ ያለ ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

በዚሁ መርሐ ግብር ላይ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሺሰማ ሸዋነካ፣ ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ ሄኖክ ከበደ እና የባንኩ የሸሪዓ አማካሪ ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር መሐመድ ዘይን ኑር ሁሴን በአዲስ መልክ የተዘጋጀውን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የንግድ ምልክት ለሕዝብ ይፋ አድርገዋል፡፡

ክብረ በዓሉ ለቀጣይ ሶስት ወራት በተለያዩ ኹነቶች የሚከበር ሲሆን በዛሬው ዕለትም ከዚሁ መርሐ ግብር ጋር ተያይዞ የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የባንኩ ሠራተኞች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተሳተፉበት የደም ልገሳ መርሐ ግብር ተከናውኗል፡፡

***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!

Picture of <p> <b>  <span style="color: #8B5E3C;">Nib International</span>   <span style="background: linear-gradient(to right, #8B5E3C, #FFA500); -webkit-background-clip: text; color: transparent; font-weight: bold;">     Bank   </span></b> </p>

Nib International Bank

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs