Internet Banking
Internet Banking

የኬሮድ የጎዳና ሩጫ ለ3ኛ ጊዜ በቡታጅራ ከተማ ተካሄደ

ንብ ባንክ ለ“ጉዞ ወደ አረንጓዴ ልማት” ለ10ኛ ጊዜ ድጋፍ አደረገ

በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ስፖንሰር አድራጊነት፣ “አረጓዴ ልማት ለሕዝቦች ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል የኬሮድ የጎዳና ሩጫ ለሶስተኛ ጊዜ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ታዳሚዎች በተገኙበት ሐምሌ 17 ቀን 2014 ዓ.ም በቡታጅራ ከተማ በድምቀት ተካሄደ፡፡

በሩጫው ላይ ከአዲስ አበባና ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የመጡ የተለያዩ ክለቦች፣ የቡታጀራ ከተማ ነዋሪዎችና የአካባቢው ኅብረተሰብ፣ የፌደራል መንግሥት፣ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ተወካዮች በዝግጅቱ ላይ ታድመዋል፡፡

በዝግጅቱ ላይ አቶ መስፍን ቸርነት የፌዴራል ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ፣ አትሌት ጌጤ ዋሚ፣ አቶ ሺሰማ ገብረሥላሴ የጉራጌ ባህልና ልማት የቦርድ ሊቀመንበርና ሌሎችም የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተው ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም ለዝግጅቱ እውን መሆን ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በተደጋጋሚ ጊዜ ስፖንሰር ሆኖ ድጋፍ በማድረጉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የጎዳና ሩጫው የመጀመሪያውና ሁለተኛው በጉራጌ ዞን ርዕሰ ከተማ ወልቂጤ፣ ሶስተኛው ደግሞ በቡታጅራ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በተያያዘም በጉራጌ ልማትና ባህል ማኅበር (ጉልባማ) አዘጋጅነት ለ10ኛ ጊዜ ሐምሌ 16 ቀን 2014 ዓ.ም በጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ የተካሄደው፣ “ጉዞ ወደ አረንጓዴ ልማት” የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ስፖንሰር ተደርጓል፡፡

በጎዳና ሩጫውና በችግኝ ተከላው መርሐ ግብር ላይ የባንካችንን ገጽታ የሚገነቡና አገልግሎቱን የሚያስተዋውቁ (ንብ ኢብርን ጨምሮ) ውጤታማ ሥራዎች በመሠራታቸው ተሳታፊዎችና የባንካችን ከፍተኛ የሥራ አመራሮች አመስግነዋል፡፡

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ

ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!

NIB BANK

NIB BANK

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

News

ታታሪውን ባንካችን ወደ ደንበኞቹ ይበልጥ ለመቅረብ  “በአዲስ መንፈስ ለላቀ ከፍታ”

Read More

You May Also like

Reports

Jobs