Internet Banking
Internet Banking

የእቴጌ ጣይቱ የገበያ አዳራሽ አክስዮን ማኅበር ተመሰረተ!

በአማራ ክልል የደብረ ብርሃን ከተማ  ነጋዴ ሴቶች ማኅበር የእቴጌ ጣይቱ የገበያ አዳራሽ አክስዮን ማኅበር ተመሰረተ፡፡

ከንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በመተባበር በደብረ ብርሃን ከተማ ኅዳር 4 ቀን 2015 ዓ.ም በድምቀት በተካሄደው የመመስረቻ ዝግጅት ላይ የከተማው ምክትል ከንቲባ፣ የአማራ ክልል ነጋዴ ሴቶች ማኅበር አባላት፣ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የሥራ ኃላፊዎች፣ የእቴጌ ጣይቱ የገበያ አዳራሽ አክስዮን ማኅበር አባላት፣ የተለያዩ ድርጅቶችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

የዕለቱ ዝግጅት፣ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ገጽታ የጎላበት፣ የብዙዎችን ትኩረት የሳበበትና የባንኩን ታታሪነት የታወቀበት እንደነበር ታዳሚዎች መስክረዋል፡፡

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ለማኅበሩ የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚያደርግ የተገለጸ ሲሆን፣ የተለያዩ አገልግሎቶቹንም አስተዋውቋል፡፡ የአክስዮን አባላቱም በበኩላቸው ከባንኩ ጋር በቋሚነት ለመሥራት ቃል በመግባት ከ200 አባላት በላይ በዕለቱ ሂሣብ ከፍተዋል፡፡

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ ከአማራ ክልል ነጋዴ ሴቶች ማኅበር ጋር በጋራ ለመሥራት የሚያስችል (የስትራቴጂክ አጋርነት) የስምምነት ፊርማ ጥቅምት 3 ቀን 2015 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ መፈራረሙ ይታወሳል፡፡

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ

ይሠሯል ከልብ እንደ ንብ!

NIB BANK

NIB BANK

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

News

ባንካችን ያጋጠመውን ጊዜያዊ ችግር በአጭር ጊዜ ለመፍታት ከደንበኞች፣ ከሠራተኞችና ከባንኩ

Read More

You May Also like

Reports

Jobs