Internet Banking
Internet Banking

የአንደኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ስብሰባ ተካሄደ!

የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የ2022/2023 የአንደኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ስብሰባ በአራት ኪሎ የባንኩ አዳራሽ ሐሙስ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም ተካሄደ፡፡

በአንደኛው ሩብ ዓመት ባንኩ ያከናወናቸው ሥራዎች ተገምግመው ጠንካራና ደካማ ጎኖች የተለዩ ሲሆን፤ በዚህም መሠረት ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ በማስቀጠል፣ ደካማ ጎኖችን ደግሞ በማረም ባንኩን ወደ ተሻለ የአፈጻጸም ደረጃ ለማሳደግ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

በዚህ ሩብ ዓመት ከወትሮ በተለየ ሁኔታ የስብሰባው ተሳታፊዎችን በቡድን በማዋቀር አስፈላጊው ውይይት ተደርጎ ተግዳሮቶችን በመለየት እንዲስተካከሉ በማድረግ እንዲሁም ወደፊት ባንኩን የተሻለ ደረጃ ላይ ሊያደርሱ የሚችሉ ጠቃሚ ሃሳቦችን በመውሰድ ተግባር ላይ ለማዋል ውሣኔ ላይ ተደርሷል፡፡ በስብሰባው ላይ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ገነነ ሩጋ፣ ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ የመምሪያ ዳይሬክተሮች፣ የዲስትሪክትና የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች የተገኙ ሲሆን ከተለያዩ መምሪያዎችና ዲቪዥን በቀረቡ ሪፖርቶች ላይ በጥልቀት ውይይት ተካሂዶባቸው ክፍተት የታየባቸው በፍጥነት እንዲታረሙ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡

በቀጣይ ባንኩ የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ሊጠቅሙ የሚችሉ አገልግሎቶች በማዘጋጀት ተደራሽ ለማድረግ የሚሠራ ሲሆን፤ በተያያዘም የዲጂታልና የኢባንኪንግ አገልግሎቶች ኅብረተሰቡ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴው እንዲጠቀምባቸው ለማድረግ በሰፊው እንደሚሠራ ተገልጿል፡፡

 

NIB BANK

NIB BANK

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

News

ባንካችን ያጋጠመውን ጊዜያዊ ችግር በአጭር ጊዜ ለመፍታት ከደንበኞች፣ ከሠራተኞችና ከባንኩ

Read More

You May Also like

Reports

Jobs