Internet Banking
Internet Banking

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የታክስ ክፍያን በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ለማሰባሰብ ስምምነት ተፈራረመ

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ የታክስ ክፍያን በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ለማሰባሰብ ጳጉሜ 1 ቀን 2014 ዓ.ም   ስምምነት ተፈራረመ፡፡

በገቢዎች ሚኒስቴር ዋና መሥሪያ ቤት በተካሄደው መርሐ ግብር ላይ ስምምነቱ፣ በባንካችን ፕሬዚዳንት በአቶ ገነነ ሩጋ በገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር በክብርት ወ.ሮ ዓይናለም ንጉሤ እና በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር በአቶ ሰለሞን ሶካ ተፈርሟል፡፡

በስምምነቱ መሠረት ግብር ከፋዮች በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ በኩል የታክስ ክፍያን በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ለማሰባሰብ የክፍያ ሥርአት መመቻቸቱ ተገልጿል፡፡

የባንካችን ፕሬዚዳንት አቶ ገነነ ሩጋ በሥነ ሥርአቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ባንኩ ለግብር ከፋዩ ማኅበረሰብ ፋይናንስ በማቅረብ እንዲሁም አስፈላጊ ሲሆን ደግሞ በአዲስ አበባና በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች ሕንጻዎችን በመገንባት ለሥራ አመቺ በማድረግ ለአገሪቱ ኢኮኖሚ አስተዋጽዎ በማድረግ ላይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ ከባንክ አገልግሎት መስጠቱ በተጨማሪ ታማኝ ግብር ከፋይ በመሆኑ በ2013 እና በ2014 በተከታታይ የግብር ዓመታት የወርቅና የፕላቲንየም ሜዳሊያ ተሸላሚ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ ጠቅሰው፤ ደንበኞች ወጪና ጊዜያቸውን በሚቆጥበው በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ አገልግሎት ግብራቸውን የሚከፍሉበት ሥርአት በመመቻቸቱ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

በፊርማው ሥነ ሥርአት ላይ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ የዓባይ ባንክና የአንበሣ ኢንተርናሽናል ባንክ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸው ታውቋል፡፡

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ

ይሠሯል ከልብ እንደ ንብ!

NIB BANK

NIB BANK

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

News

ባንካችን ያጋጠመውን ጊዜያዊ ችግር በአጭር ጊዜ ለመፍታት ከደንበኞች፣ ከሠራተኞችና ከባንኩ

Read More

You May Also like

Reports

Jobs