Internet Banking
Internet Banking

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ሽልማት አበረከተ!

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ሽልማት አበረከተ!

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ በጉራጌ ዞን በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የገንዘብ ሽልማት አበረከተ፡፡

በዞኑ መቀመጫ ወልቂጤ ከተማ መጋቢት 23 ቀን 2015 ዓ.ም በተካሄደው ሥነ ሥርአት ላይ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 40 ተማሪዎች ለእያንዳንዳቸው የብር 10,000.00 (ብር አስር ሺህ) በድምሩ ብር 400,000.00 (ብር አራት መቶ ሺህ) ድጋፍ አድርጓል፡፡

ባንኩ፣ ከዞኑ ጋር ተቀራርቦ የሚሠራ ሲሆን በተለያዩ ጊዜያት ለባንኩ ለሚቀርቡ የድጋፍ ጥያቄዎች አዎንታዊ ምላሽ እየሰጠ ሲሆን፤ በየዓመቱ የሚካሄደውን የጉራጌ ባህልና ልማት የአረንጓዴ ዘመቻን ለበርካታ ዓመታት በመደገፍ ላይ እንደሆነም ይታወቃል፡፡

በአገሪቱ ውስጥ ካሉ የግል ባንኮች ግንባር ቀደም የሆነው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ  ከ23 ዓመታት በላይ ባሳለፈው የባንክ አገልግሎት፣ ከበርካታ ደንበኞቹ ጋር ተቀራርቦ በመሥራት ብዙዎችን በመደገፍ መሠረቱን ያጸና መሆኑን በርካቶች ይመሰክሩለታል፡፡

ታታሪው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ጠንካራ የሥራ ባህል ባለው የጉራጌ ዞን ውስጥ በርካታ ቅርንጫፎችን በመክፈት የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን በባንኩ ራዕይ ላይ በግልጽ በሰፈረው መሠረት በደንበኞች አገልግሎት የልህቀት ከፍታ ላይ በመድረስ በኢትዮጵያ መሪ የንግድ ባንክ ለመሆን የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡

ባንካችን የደንበኞችን ፍላጎትና ምርጫ ሊያሳድጉ የሚችሉ የተለያዩ አማራጮችንም በማቅረብ ይታወቃል፡፡ በቅርቡም የአገልግሎት አድማሱን ሊያሰፉ የሚችሉ ንብ ማር፣ ንብ ማኅበራዊ፣ ንብ ልገሳ እና ንብ የሥራ ፈጣሪዎች የቁጠባ ሂሣብ አይነቶችን ለደንበኞች ሥራ ላይ አውሏል፡፡ በተያያዘም ንብ ኢብርን ሥራ ላይ በማዋል ለደንበኞች ምቹና የተቀላጠፈ አገልግሎት በመስጠት ታታሪነቱን በማስመስከር ላይ ይገኛል፡፡

ባንካችን ኅብረተሰቡን ጠቅሞ ራሱንም መጥቀም እንዲችል የተለያዩ ሕንጻዎችን በመገንባት ለከተሞች ዕድገትም ሆነ ለአገር ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የራሱ የሆነ አስተዋጾ ለማድረግ ድርሻውን እየተወጣ ነው፡፡ ለዚህም እንደ አብነት ሊጠቀሱ የሚችሉ በአዲስ አበባ ከተማ ከኮሜርስ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ራስ አበበ አረጋይ ጎዳና የሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤትና የአራት ኪሎ ሕንጻ፣ በክልል ከተሞች እዚህ ወልቂጤ ላይ፣ በዱከም በሆሳዕና እንዲሁም በቅርቡ ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ ያለው የሐዋሳው ባለመንታ ሕንጻ በማስገንባት በአገር አቀፍ ደረጃ አሻራውን አሳርፏል፡፡

ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ

ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!

NIB BANK

NIB BANK

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

News

ባንካችን ያጋጠመውን ጊዜያዊ ችግር በአጭር ጊዜ ለመፍታት ከደንበኞች፣ ከሠራተኞችና ከባንኩ

Read More

You May Also like

Reports

Jobs