“25 አመታት በታታሪትና በአገልጋይነት” በሚል መሪ ቃል ለወራት በተለያዩ ኩነቶች ሲከበር የነበረው የባንካችን የሩብ ምዕተ ዓመት የምሥረታ በዓል በማርች ባንድ በታጀበ የባንካችን ሠራተኞች የእግር ጉዞ ሥነ ሥርዓት ተጠናቋል፡፡
በእግር ጉዞው የማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ የዲሬክተሮች ቦርድ ሊቀ መንበር ተወካይ አቶ አበራ ሽሬ እና የባንካችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሄኖክ ከበደ ተገኝተው መልዕክት አስተላልልዋል፡፡
በዚህም መልዕክታቸው የቦርድና ማኔጅመንት አባላት ከምንጊዜውም በተለየ ቁርጠኝነት ሰርቶ በማሰራት የአዲሱ ታሪክ ምዕራፍ አካል ለመሆን መትጋትና ባንካችን ደንበኞቹን፣ ባለአክሲዮኖቹንና ሠራተኞቹን የሚያኮራ እንደሆነ ማረጋገጥ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ባንኩን ለ25 ዓመታት ላገለገሉ ሰራተኞች የእውቅናና የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶ የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል፡፡