Internet Banking
Internet Banking

የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዲሬክተሮች ቦርድ አመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት መርሐ-ግብር አከናወነ።

የቦርዱ ሊቀመንበር አቶ ሺሰማ ሸዋነካ እና የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር እመቤት መለሰን ጨምሮ የቦርዱና የባንኩ ማኔጅመንት አባላት በመርሐ-ግብሩ ተገኝተዋል።

 

በመድረኩ በተገባደደው ዓመት የኮርፖሬት አፈፃፀም፣ የውስጥ ኦዲት፣ የሪስክ እና ኮምፕሊያንስ እንዲሁም የሕግ ጉዳዮች አፈፃፀሞች ዙሪያ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

 

በዚህም ባንኩ በተለያዩ ቁልፍ መመዘኛዎች የተሻለ የአፈፃፀም ውጤት ማስመዝገብ የተቻለባቸው መስኮች ተለይተው ቀርበዋል፡፡

 

በዚህም ከነበሩ ተግዳሮቶች አንፃር በሁሉም ዘርፎች የተገኙ ውጤቶች አበረታች መሆናቸውን የምክክር መርሐ-ግብሩ ተሳታፊ የቦርድ እና የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም የዲስትሪክት ዳይሬክተሮች በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

 

በ2017 የሥራ ዘመን እነዚህን እመርታዎች በሌላ ውጤት በማጀብ ባንኩ ያስቀመጠውን የለውጥ ፍኖተ ካርታ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባም ከቦርዱ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡

 

ለዚህም በሰራተኛው ዘንድ ከፍተኛ የሥራ ባህል ለውጥ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ትኩረት ተሰጥቶት ውይይት ተደርጎበታል፡፡

 

መረጃውን ለሌሎች ስለሚያጋሩ እናመሰግናለን!
***
ይሠሯል ከልብ፣ እንደ ንብ!

 

 

NIB BANK

NIB BANK

Committed To Services Excellence

Share this post with

Recent Posts

You May Also like

Reports

Jobs